ሰባቱ የስኬት ምስጢራት

ሰባቱ የስኬት ምስጢራት

Author/s: ዩኒቲ መፅሐፍ መደብር ፋሲካ

Subjects

Self development, Management

Published Year

2015

Book Type

Ebook

Summary

ይህ "7ቱ የስኬት ምስጢር" የሚለው መፅሐፍ በኒውዮርክ ታይምስ ምርጥ የመፅሐፍ ሽያጭ ሰንጠረዥ ላይ ከ 40 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች ሊሸጥ ከመቻሉም በላይ ፣ የሃያኛው ክፍለ ዘመን ከፍተኛ ተወዳጅነት እና ተቀባይነት ያለው ቁጥር አንድ መፅሐፍ ሆኖ እስካሁን ድረስ ቆይቷል። እስከዛሬ ከተፃፉት እጅግ በጣም አነቃቂ እና በሰዎች ህይወት ላይ ምርጥ በሆነ መልኩ በጎ ተፅዕኖን መፍጠር ከቻሉ መጽሐፍት ውስጥ አንዱም ነው።ይህ የ 7ቱ የከፍተኛ ውጤታማ ሰዎች ልማድ የሚለው መፅሐፍ ለባለፉ ለሦስት አስርት ዓመታት የ አንባቢዎችን ቀልብ ይዞ በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማ ያደረጋቸውን መንገድን ያሳየ መፅሐፍ ነው።መፅሐፉ የፕሬዚዳንቶችን እና ዋና ሥራ አስፈፃሚዎችን ፣ የአስተማሪዎችን ፣ የወላጆችን እና በሁሉም ዕድሜዎች እና የሙያ መስክ ውስጥ የሚገኙትን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወትን ለውጧል፣በመለወጥም ላይ ይገኛል፣ ለወደፊቱም ይለውጣል ። ይህ የ መፅሐፉ የ 30 ኛ ዓመቱ ክላሲክ ዕትም ደግሞ የ ሰባቱን ልማዶችን ጥበብ ደራሲው ስቴቨን ኮቬይ በድሮው ዕትም ላይ ጥቂት ከዘመኑ ጋር የሚሄዱ ወሳኝ የሆኑ ነጥቦችን በመፅሐፉ ውስጥ አካቷል። እነዚህ 7 ቱ የስኬት ምስጢራት በጣም ተቀባይነትን ያገኙ ስለሆኑ ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች የ ዕለት ከ ዕለት አስተሳሰብ ጋር ተዋህደዋል። እንዴት? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ ባህሪያቱ በጣም ስኬታማ እና ሕይወትን ውጤታማ ሆነን እንድንኖር ስለሚያደርጉን ነዋ!

0.0 (0 reviews)