አባ የሎስ
Summary
ይህ መፅሐፍ በባህሪው "የእንስሳት ዕድር "ከተሰኘውና ዓለም አቀፍ አድናቆትን ከተቸረው የጆርጅ ኦርዌል ስራ ጋር አምሳያነት ያለው ቢመስልም በቅርፁ በይዘቱም ይሁን ባቋተው ሀቅ ይለያል ። በእርግጥም "አባ የሎስ" ምፀታዊ ዘይቤያዊና ምሳሌያዊ ቃናዎች በቃላት ቀለም ተስለውና ተቀምመው ስለቀረቡበት የራሱ መልክና ደም ግባት አለው ። "አባ የሎስን" በጥሞና ላነበበ ደራሲ አንዳርጌ መስፍን ይህንን መፅሐፍ ከማሰናዳቱ በፊት በቤትና በዱር እንስሳት አልፎም በአእዋፋት ዙሪያ ለአመታት ጥናት ማካሄዱን መገንዘብ አይከብደውም ። የአማርኛ ቋንቋ ቃላቶች ነገሮችን የመግለጽና የማብራራት አቅም የት ድረስ ሊሆን እንደሚችል በመገመት መደመማችን አይቀርም ። በዚህም ይሁን በሌሎች መስፈርቶች ይህ መፅሐፍ የደራሲው ግሩም ብዕራዊ በረከት እንደሆነው "ጥቁር ደም" በኢትዮጵያ ስነ ጽሁፍ መስክ የሚኖረው ሥፍራ እንደተጠበቀ ሆኖ በዘርፉ አዲስ ምርምር እንዲካሄድ መጋበዙ አያጠራጥርም ። ሠለሞን ለማ ገመቹ የጀግና ወሮታ መፅሐፍ አዘጋጅ