በየካቲት ጣጣችን ክትት

በየካቲት ጣጣችን ክትት

Author/s: ምሕረት አቤሴሎም

Subjects

History, Politics, Literature

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

አገራችን ኢትዮጵያ የታሪክ ሀብታም ናት። ከዚህ ሰፊ ሀብቷ ልጆቿ ሁሉ ልንቋደስ ይገባናል። እንደ አለመታደል ሆኖ ይህ መጽሐፍ የተጻፈበት ዘመን እውነተኛው የኢትዮጵያ ታሪክ በብዙ የሐሰት ታሪክ መበረዝ የደረሰበት፣ በትምህርት ቤትም እንደሚገባ መሰጠት የቆመበት፣ ትውልዱ ታሪኩን በአግባቡ እንዳይረዳ፣ መልካሙን አጠንክሮ፣ የሚታረመውን አርሞ የወደፊቱን ነገ በአግባቡ እንዳይገነባ፤ ታሪኩን የሚያውቅበትን ዕድል የተነፈገበት ነው። ልጆቻችን ታሪካቸውን ተምረው አገራቸውን የሚወዱበትን ዕድል የተነፈጉበት ዘመን ነው። ይህን ለማረቅ የዚህ ዘመን ወላጆች ብዙ ይጠበቅብናል። ሶፊያና ኅሊና በየአሉበት አገር በዓድዋ ላይ ሲነገር የሰሙት የሐሰት ትርክት አሳዝኗቸዋል። ስለ ታሪኩ እና ለዓለም ስላበረከተው ትሩፋት በሚገባ ለመረዳትና ለሌሎችም ለማሳወቅ ዓላማ ይዘው የጥናት ጽሑፍ ለማቅረብ ይነሳሉ። ጥናቱን ለማዘጋጀት በሚያደርጉት ጥረት ስለ ዓድዋ እስከዛሬ ሰምተው የማያውቁትን አስደናቂ ታሪኮች ያገኛሉ። እነዚህን አስደናቂ ታሪኮችና ትሩፋቶች አካትተው ያቀረቡት ጥናት ለሽልማትና ለብዙ አድናቆት ያበቃቸዋል። ዓድዋ ቢነገር ቢነገር የማያልቅ፣ ከአንድ ጦርነት ማሸነፍና መሸነፍ በላይ የብዙ ምስጢር ባለቤት የሆነ ድል ነው። የዚህ መጽሐፍ ዓላማ የዓድዋን ታሪክ ከባሕር በጭልፋ እንደ መቆንጠር ያለ፤ ለነገ አገር ተረካቢ ወጣት ልጆቻችን መንገር እና ድሉ ለሰው ልጆች ያለውን ትሩፋት በጣም በጥቂቱ ማንሣት ነው። ልጆቻችን ታሪካቸውን የበለጠ የማወቅ ጉጉት እንዲፈጠርባቸው መጫር ነው። በርካታ ሥዕሎችን ባካተተችው በዚህች መጽሐፍ ውስጥ ስለ ዓድዋ አስደማሚ ታሪኮችን ያገኛሉ። ይህችን አንብበው ስለ ዓድዋ በአላቸው ግንዛቤ ላይ ጥቂት እንደሚጨምሩና ስለ ዓድዋ እና ሌሎች የአገራችን ታሪኮች በሰፊው የተጻፉ መጻሕፍትን ለማንበብ እንደሚነሣሡ ተስፋዬ ነው። መጽሐፉ ለወጣት ልጆቻችን ታስቦ ቢዘጋጅም በየትኛውም እድሜ ክልል ያሉ አንባቢያን በርካታ ቁም ነገሮችን የሚያገኙበት፤ ወላጆች፣ ምሑራን ሁሉ ትውልዱ ታሪኩን፣ ባህሉን፣ ማንነቱን እንዲያውቅ በማድረግ ረገድ የበለጠ እንዲሠሩ ቂጭት የሚፈጥር፣ የሚያነሣሣ መጽሐፍ ነው። ዶክተር አለማየሁ አምቦ

0.0 (0 reviews)