ንፍታሌም

ንፍታሌም

Author/s: አብርሃም ቃሉ

Subjects

Literature

Published Year

2025-12-08

Book Type

Ebook

Summary

........ናታየ ቀድመኸኛል ብየ ነበር ፤ ግን ደሞ መንገዱን አላመንኩትም ፤ ወጪ ወራጅው ውስጥ አይኖቼን ተክየ እየፈለኩህ ነበር ፤ የእኔ ውድ እንዴ ነህ ? አለች ፤ ኬብሮን ። የጥጥ ፍልቃቂ የሚመስሉ ጥርሶቿን ብልጪ እያደረገች ። ፍንድቅ ፣ ፍንድቅድቅ ባለ የናፍቆት ሰላምታ ፤ በውብ ፈገግታ ታጅበው ተቃቀፉ ። ኬብሮን ከተቃቀፉበት ትንሽ ለቀቅ አድርጋ እረጅም ሰጎን የሚመስለው አንገቱ ስር ተለጠፈች ፤ በስንደዶ እረጅም አፍንጫዋ ማራኪ ጠረኑን ማገችው ፤ የማር ጠረን ፣ ለዛውም የወለላ ማር በህሊናዋ እየተዥጎደጎደ መላሰውነቷን አዳረሰው ፤ አጥለቀለቀው ፤ የአይኖቿ እንባ በናታን ደረት ላይ ኮለል አሉ ፤ አልታወቃትም .. ናታን ቀና አድርጎ በእጆቹ መዳፍ ጠራረገላት ፤ ኬብሮሜ ሆድ ብሶህ ሆድ አታስብሰኝ አላልሽኝም ፤ እና ለምን ሆድ ብሶሽ ሆድ ታስብሽኛለሽ ? ውስጡ ...........፤

0.0 (0 reviews)