አትሄጂም

አትሄጂም

Author/s: እመቤት መንግስቴ

Subjects

Fiction, Literature, Philosophy

Published Year

2009 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

"ይህንን መፅሀፍ ለምን ፃፍሸው?" ተብዬ ተጠይቄ ነበር። መፅሀፉ የተለያዩ አጫጭር ታሪኮችን ቢይዝም፣ አላማው በልበ-ወለድ ትረካ አሳብቤ ወገኖቼን ማስተማር እና የተለያዩ የአለም ገጠመኞቼን በማውጋት አንባቢዎቼን እያዝናናሁ አእምሯቸውን መጎንተል ነው። ተነጋግረን ልንፈታቸው ወይም በጊዜ ልናስወግዳቸው የምንችላቸውን ብዙ ችግሮች በዝምታ አፍነን ስናባብሳቸው ስላየሁ፣ ምናልባት ይህንን መጥፎ ባህል ለመለወጥ ይረዱ ይሆናል በሚል ተስፋ ነው ተረቶቼን ለማሳተም የመረጥኩት። ይህንን ስል፣ እኔ የተሻለ አውቃለሁ ወይም የማስተማር ችሎታ አለኝ ብየ ሳይሆን፣ እኛ ተሞክሯችንን ብንወያይና ብናዋይ፣ መጭው ትውልድ የኛን ስህተት ደግሞ እንዳይሰራ ይማርበት ይሆናል ከሚል እምነት ተነስቼ ነው። ሁለተኛው ሀሳብ ደግሞ፣ ከአያቶቻችን የወረስነው ችግርን ብቻ አይደለም። ለረጅም ዘመን ሞክረውና አጣርተው የተውልን መፍትሄዎችም አሉ። ባህላችን እነዚህ መፍትሄዎች የተፃፉበት ህያው ሰሌዳ ነውና ዞር ብለን እንመልከተው፣ አባት እናቶቻችን ለዘመናት እንደተገለገሉበት ሁሉ እኛም እንጠቀምበት፣ እናክብረው፣ ይዘነውም ወደፊት እንራመድ፤ ለማለት ነው። እመቤት መንግሰቴ

0.0 (0 reviews)