ዓለማየሁ እሸቴ
Summary
አሀገሩን አጥብቆ በመውደድ እና ለሀገሩ ከልብ በመስራት ለብዙ ከያንያን አርአያ የሆነው አለማየሁ እሸቴ ማረፉን ሰምቼ እጅግ አዝኛለሁ ።ስራዎቹ ኢትዮጵያን ከፍ እንዳደረጉ ይኖራሉ ።ለኢትዮጵያ የሰራ ያርፋል እንጂ አይሞትም ። ዶክተር አብይ አህመድ (የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከፍ ያለ ስም ያላቸውን አቀንቃኞች ስናወሳ ከፊት ከምናገኛቸው ሰዎች መካከል አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ዋነኛው ነበር ።አለማየሁ እሸቴ ከዘፈኖቹ ባሻገር እንደ ይድነቃቸው ተሰማና ፍቅሩ ኪዳኔ አራዳ ላይ የነገሰ የፒያሳ ንጉሥ ነበር ።ይህንንም ታሪክ ከመፅሃፉ ደራሲ ጋዜጠኛና ደራሲ (ጸሐፊ ጥበብ ) ወሰን ደበበ ማንደፍሮ በተለመደው የአተራረክ መንገዱ ብሎም በምስል ከሳች ብዕሩ አለማየሁን ከነ አለባበሱና ከነፈረሱ ይተርክልናል ። መምህር ማርቆስ ጌታሁን "እኔ አርእስቱን ተናግሬ እወርዳለሁ አንተ በተከለከለው ግጥም ዝፈን " ተባባልንና የእለቱ መድረክ መሪውም እኔ ስለነበርኩ አስተዋዋቄ ስወርድ ደፋሩ አለማየሁ የሳንሱር መቀስ በበላው ግጥም ዘፈነው ። ተስፋዬ አበበ ( የክብር ዶክተር ) አለማየሁ አለም አቀፍ ዘፋኝ ነው ።አለማየሁ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የዘመናዊ ታሪኳ ዋልታና ማገሯ ነው ። አለማየሁ የሀገራችን ሙዚቃ አለም አቀፍ ገጽታ የቀየረ የሮክ ኤንድ ሮል ሰንደቅ ነው ። ማህሙድ አህመድ (የክብር ዶክተር ) ጊታር ሲጫወት ብዙ ሰው አላየው ይሆናል የድራም እውቀትን ብዙ ሰው አያውቅ ይሆናል ፣የማቀናበር ሃሳቡንና ኦርጋን የመጫወት አቅሙን ብዙ ሰው አልተረዳለት ይሆናል እንጂ እነዚህ ያልታዩና በድምፃዊነቱ የተሸፈኑ ከጀርባ ያሉ ከፍተኛ ብቃቶቹ ናቸው ። ሰርፀፍሬ ስብሀት (ሙዚቃ ባለሙያ ) አሌክስ ከልቡ የስሜቱን ነው የሚዘፍነው ። ራሱን ህይወቱን ነው የሚያንጎራጉረው ።የተሰጠውን ብቻ አንጠልጥሎ ወደ መድረክ አልያም ወደ ስቱዲዮው አይገባም ። የዘፈኑ ይዘት ጠንካራ መልእክት ካልያዘ ፣ ሰው ሰው የሚሸት ፣ችግርን የሚጋራ እና ቁስሉን የሚያክም ካልሆነ አልዘፍንም ምን ይጠቅማል ? ነው የሚለው ። ከአሌክስ ጋር በህይወት እያለ የምንወያየውን ሃሳብ ሳሰፍር ታላቅ ደስታ ይሰማኛል ። ሰዓሊ ልዑልሰገድ ረታ So sad to hear of the passing of Ethiopian musician "Elvis" Alemayehu . The world 's loss is Heaven 's gain Where the music will no doubt improve ! Tibor Nagy