አፄ ቴዎድሮስ 2

አፄ ቴዎድሮስ 2

Author/s: ዩኒቲ መፅሐፍ መደብር ፋሲካ

Subjects

History

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

በአንድ ወቅት አንዲት ሴት አርባ ክንድ ርዝመት ያለዉ መቀነት ሰርታ ለአጼ ቴዎድሮስ በስጦታ አቀረበችላቸዉ ፡፡ አጼ ቴዎድሮስም በስጦታዉ ተደስተዉ ሸለሟት ፡፡ይህንን ታሪክ የሰማች አንዲት መልከመልካም ሴት ‹‹ለዚያች መልከ ጥፉ አጼ ቴዎድሮስ የሸለሙ የእኔንማ ቁንጅና ሲያዩ የበለጠ ይሸልሙኛል ››በማለት ወደ ንጉሱ ሄደች፡፡እሳቸዉም ‹‹ሙያሽ ምንድነዉ እቱ ብለዉ ጠየቋት ፡፡ እሷም ሴተኛ አዳሪ ነኝ ፡፡ ሌላ ሙያስ የለኝም ብላ መለሰችላቸዉ ፡፡አጼ ቴዎድሮስም እግዚአብሄር ሁለት እጆች የፈጠረልሽ እንድትሰሪባቸዉ ነበር ፡፡አንቺ ግን እጆችሽን የምትጠቀሚያቸዉ እንጀራ ለመቁረስ ብቻ ስለሆነ አንዱ ይበቃሻል አሏትና አንድ እጇ እንዲቆረጥ አዘዙ ፡፡በዚህ ወቅት የነበሩ አዝማሪዎች እንዲህ በማለት ይገጥሙ ነበር፡፡ ማረስ ይሻላል መገበር እጅ እግር ይዞ ለመኖር አላርስም ያሉ አልነግድ ተመላለሱ እንደግንድ (ተረክ ቁጥር 68 ገጽ 55-560) አንድ ብረት ቀጥቃጭ አጼ ቴዎድሮስ ፊት ይቀርብና በጸና ታማ ለመሞት በምታጣጥር ሚስቱ አጠገብ መሆን ይችል ዘንድ ለጥቂት ቀናት የስራ እረፍት ፈቃድ እንዲሰጡት ይጠይቃቸዋል ፡፡ አጼ ቴዎድሮስም በሰዉየዉ ሁኔታ ልባቸዉ ተነካና በጣም ይወዷት የነበረችዉን ማቿን ሚስታቸዉን በማሰታወስ አቀርቅረዉ ማልቀስ ጀመሩ፡፡ በአንድ ወቅት አጼ ቴዎድሮስ ምርኮኛዉን የሸዋዉን ምንሊክ ‹‹አባትህ ምን አዉርሶህ ሞተ ብለዉ ጠየቁት ፡፡አስራ ሁለት አመቱ ታዳጊ ምንሊክም አንገቱ ላይ ያሰረዉን ክታብ አሳያቸዉ ፡፡ ክታቡም ሲፈታ ብዙ ሀብትና ንብረት የተከማቸዉን ቦታ እንደካርታ የሚጠቁም ሆኖ ተገኘ፡፡ አጼ ቴዎድሮስም በዚህ እየተመሩ በመሄድ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የተደበቀ ሃብትና ንብረት አገኙ (ገጽ 42 ተረክ ቁጥር 50) በአንድ ወቅት ደጃዝማች ተድላ ጓሉ ሞቱ ፡፡አጼ ቴዎድሮስም የደጃዝማች ተድላን መሞት ሲሰሙ አዘኑ ደነገጡም ፡፡ ምክንያታቸዉ ደግሞ አዋቂዎች ተድላ ጓሉ ሲሞት አንተም ተከትለኸዉ ትሞታለህ ብለሃቸዉ ስለነበረ ነዉ (ተረክ ቁጥር 54 ገጽ 45)

0.0 (0 reviews)