የሻማ ብርሃን ፪

የሻማ ብርሃን ፪

Author/s: ከፈለኝ ዘለለው

Subjects

Non Ficition, Self Development, Philosophy, Communication

Published Year

2014 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

"የሻማ ብርሃን ፪" ብዙዎቻችን ፀጋ - አልባ እንደሆንን እናስባለን፡፡ ያለንም ከሌሎች ያነሰ ሆኖ ይሰማናል፡፡ አልታደልኩም ተበድያለሁ! የለኝም ሌጣ ነኝ በሚሉ ራስን አኮሳሽ ጥቁር ሀሳቦች ተጠፍረናል፡፡ በዝቅ አድራጊ አስተሳሰቦች ተወረናል፡፡ በሌለን ነገር ማማረርን እንጂ ባለን ነገር ማመስገንን አልተለማመድንም፡፡ እኔ ግን ትልቁ የሚኖረኝ ከትንሹ መነሳት ስችል እንደሆነ አምናለሁ፡፡ አምኜም እኖራለሁ፡፡ በመኖሬም እነሆ "የሻማ ብርሃን ፪"ን አበረከትኩላችሁ፡፡ ባጫጭር መስመሮች ረጃጅም መልዕክቶችን ያስተላለፍኩበት አምስተኛ መፅሐፌ ነው፡፡ በዚህ መፅሐፌ ውስጥ የተካተቱ ሥራዎች ፤ በተለያዩ አጋጣሚዎች በሕይወት መንገዴ ላይ የሚሸነቁጡ ጉዳዮች ሲያጋጥሙኝ ፤ ብዕሬን ከወረቀት አወዳጅቼ የከተብኳቸው ፤ "በሁሉም ዘመን ለሁሉም ሰው" አስፈላጊ የሆኑ የብዕር ጠብታዎቼ ናቸው፡፡ አጫጭር የሚመስሉ ነገር ግን ረጃጅም ሀሳቦችን ከሁለገብ ጭብጦች ጋር አቆራኝተው አዝለዋል፡፡ ገደብና ወሰን ሳይጋርዳቸው በርካታ እይታዎች ላይ ያውጠነጥናሉ፡፡ እየነኩ ያብከነክናሉ! እየጎሸሙ ያሳስባሉ፡፡ እየጎነተሉም ያነቃሉ፡፡ ለተጨነቀ ውስጠት እፎይታን ፤ ለተከፋም ማንነት የሀሴት መንገድን ይጠቁማሉ፡፡ ለተሰላቸና በተስፋ መቁረጥ ባሕር ውስጥ ለሚቧችር ሰውነት መረጋጋትን ይለግሳሉ፡፡ እያበረቱ የሚያጀግኑ ፤ አጀግነውም እያፀኑ የታመመ መንፈስን የሚያክሙ የብዕር ትሩፋቶቼ ናቸው፡፡ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ያሉ ስራዎቼን ደጋግመው ባነበቧቸው ቁጥር ለጭንቀትዎ መላ ፤ ለገጠመዎት የብስጭት ሀሩርም ጥላ ያገኛሉ፡፡ "የሻማ ብርሃን ፪" መፅሐፌ በውስጥዎ ለታፈኑ ጭቁን ሀሳቦች አጉልቶ የሚጮህ የጥበብ ፍሬዎች ስብስብ ነው፡፡

5.0 (1 reviews)