ስኬታማ አስተሳሰብ

ስኬታማ አስተሳሰብ

Author/s: ዩኒቲ መፅሐፍ መደብር ፋሲካ

Subjects

Self Developement

Published Year

2004 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ለቁርጠኝነት ያለን ተፈጥሯዊ ፍላጎት ያለመቆራኘትን ውጤት አደገኛ ያደርገዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሳንቆራኝ የተቆራኘን ይመስለናል፡፡ ለምሳሌ ቴከኖሎጂ ሳንገናኝ የተገናኘን እንዲመስለን ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ቴክኖሎጂ ባሰከረው ዓለም ተግባቢነትን ከመገናኘትና ከመቆራኘት ስሜት ጋር አምታትተነዋል፡፡ ከኮምፒውተር ስክሪን ፊት የሌሎችን ምስል ስላየን የእኛም ከእነርሱ ዘንድ ስለታየ ብቻ ታይተናል ወይም ተሰምተናል ማለት አይደለም፡፡ በእርግጥም ዛሬ ፤ ዛሬ ከምናስብላቸው ሰዎች ጋር ገጽ ለገጽ ተገናኝተን ከምናሳልፈው ጊዜ ይልቅ ‹‹ በፌስቡክ ላይ የምናሳልፈው ይበልጣል፡፡ ብዙ ጊዜ ወደ ሬስቶራንት ስገባ ወላጆችም ልጆችም በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው _ ሁሉም የየግል ስልኮቻቸውን በመነካካት መልዕክት ከሌሎች ጋር ሲለዋወጡ ወይም በተቀረፁ ጨዋታዎች ሲዝናኑ እመለከታለሁ፡፡ ታዲያ የእነርሱ አብሮ መቀመጥ ትርጉሙ ምንድር ነው? ሐፍረት፣ ትንሽ እንደሆንን፣ እንከን ያለብን መሆናችንን እንዲሁም ብቁ አለመሆናችን እንዲሰማን የሚያደርግ በሠራ አካላችን የሚሰራጭ እንደረመጥ የሚፋጅ ስሜት ነው፡፡ከሐፍረት የማገገም ብቃትን፣ ለሐፍረት ዕውቅና በመስጠት ትክክለኛ ማንነታችንን ዋጋ ያለሽነታችንን እንዳጠበቅን ወደ ፊት የመጓዝ ችሎታን ለማዳበር የምንፈልግ ከሆነ ሐፍረት ለምን እንደሚገጥመን ማውራት አለብን፡፡ ስለ ሐፍረት በግልጽ መነጋገር የምንኖርበትን፣ የምናፈቅርበትን፣ ልጆች የምናሳድግበትንና ግንኙነት የምናዳብርበትን መንገድ ሊለውጠው ይችላል፡፡ ትክከለኛነት ሁልጊዜም አስተማማኝ ምርጫ አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከመወደድ ይልቅ እውነተኛ ማንነትን ለማንፀባረቅ መምረጥ ከምቾት ቀጠና ሊያስወጣ ይችላል፡፡ አንድ ሰው ከአደጋ ጋር ሲጋፈጥ፣ አዲስና ያልተወደዱ ሐሳቦችን ሲያቀርብ ወይም እንግዳ የሆኑ ነገሮችን ሲሞከር መተቸት በጣም ቀላል ነው፡፡ ክፋት፣ ርካሽ፣ ቀላልና ተትረፍርፎ የሚገኝ ነው:: እውነተኛና ጀግና ለመሆን በምንጥርበት ጊዜ የሚደርሱብን ውግዘቶች እውነተኛ ባይሆኑ እንኳ ከፋት የሚጎዳ መሆኑን ማስታወስ አለብን፡፡ ከተለመደው በተቃራኒ ስንጓዝ አንዳንድ ሰዎች ሥጋት ያድርባቸውና አጥንታችን ድረስ ዘልቆ ሊጎዳን በሚችል አቅጣጫ ሊመጡ ይችላሉ- ስለ አካላዊ ገጽታችን፣ ስለ ፍቅር ሕይወታችን አሊያም ስለ ልጅ አያያዛችን በመጥቀስ ያጠቁናል፡፡ ሁላችንም ብንሆን ወደ ኋላ አፈግፍገን ከእጥረት አስተሳሰብ ነጻ ለመውጣት ምርጫ አለን፡፡ አንድ ጊዜ ከእጥረት አስተሳሰብ ከተላቀቅን በበቂ ሁኔታ የመገኘትን አስገራሚ እውነታ እናገኛለን፡፡ በበቂ ሁኔታ መገኘት ስል ስለማንኛውም ነገር መጠን መናገሬ አይደለም፡፡ በበቂ ሁኔታ መገኘት ከድህነት በሁለት እርምጃ የተሻለ ወይም ከመትረፍረፍ አንድ ደረጃ ዝቅ ያለ አይደለም፡፡ በቂነት ፈጽሞ ከመጠን ጋር የተያያዘ አይደለም፡፡ በቂ እኛ በራሳችን በቂ የመሆናችን ተሞከሮ ነው፣ የምንቀርፀው ዐውድ ነው፣ ድንጋጌ ነው፣ ማወቅ ነው፡፡ መንፈሳችሁን የሚያነሳሱ ሥራዎችን በዝርዝር ጻፉ፡፡ ተግባር ተኮር አትሁኑ፡፡ ስለ ኑሮ ወይም ገንዘብ ስለማግኘት አታስቡ የምትወድዱትን ነገር ስለመሥራት አስቡ፡፡ ትርጉም ያለው ሥራ ለመሥራት የግድ መደበኛ ሥራችሁን ማቆም የለባችሁም፡፡ እንዲሁም መደበኛ ሥራችሁም ቢሆን ልብ ብላችሁ አላሰባችሁት ይሆናል እንጂ ለእናንተ ትርጉም ያለው ሥራ ሊሆን ይችላል፡፡ ለእናንተ ትርጉም ያለው ምንድር ነው?

0.0 (0 reviews)