አርበኛና ባንዳ በእናት ጓዳ

አርበኛና ባንዳ በእናት ጓዳ

Author/s: መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን

Subjects

History, Politics, Non Ficition

Published Year

2008 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

የሃገሬ ሁኔታ እኔንም እንደ አንድ ዜጋ ያሳስበኛል። በጠና ታምሜ ያልጋ ቁራኛ ሆኘ እንኩዋን የህሊና እረፍት ማግኘት አልቻልኩም ተጨማሪ ዉጋት ሆኖ ያስጨንቀኛል፡፡ ደራሲዉ የተከዜ ዉኃ ገና ከሩቅ ስናየዉ ቀይ ቀለም የተበጠበጠበት ይመስል ነበር፡፡ ቀረብ ብለን ስናየዉ ግን ከዳር እስከ ዳር ሬሳ ሞልቶታል ፡፡የሰዉ ሬሳ የእንስሳት ሬሳ ያራዊት ሬሳ እግር ከራስ ተቆላልፎ አንዱ ባንዱ ላይ ተደራርቦ ተከምሯል። ይህንን ሳይ ዉኃ ጥሜ ተቆረጠ፡፡ አንጋፋወ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ጎሰኝነት ዛሬ ባገራችን አስከፊ ደረጃ ላይ ከመድረሱ የተነሳ የጭንቅላት ካንሰር እስከ መሆን ደርሷል። ይህንን ሀቅ የሚያስተባብል አንድም ባለ ስልጣን አይኖርም ፡፡ ‹‹ አማራ በባዶ እግሩ እየሄደ ግን ደግሞ የትምክህት ልሃጩን እያንጠባጠበ የሚናገረዉ መርዝ ነዉ ። ›› (አንድ የብአዴን ከፍተኛ ባለ ስልጣን ያማራን ህዝብ ከዘለፋዉ ተቀንጭቦ የተወሰደ፡፡) ‹‹ትግሬ ገዳይ (አማራ ቀደም ባሉት ዘመናት ) ‹‹አማራ ገዳይ (ትግሬ በዚህ ዘመን ) ‹‹ ይህንን ሁሉ ዘመን መስዕዋትነት ከፍለን ዳገት ቁልቁለት የወጣንበትና የወረድንበት ታሪካችን ዛሬ ገደል ገብቷል። ባማራ ነፍጠኛነት አስወግዞናል፡፡ ከእንግዲህ ስለ አንድነትና ስለ ኢትዮጵያዊነት ማሰብ መጃጃል ነዉ። ›› የናቱን ቤት ሁለት ጊዜ አቃጥሎ እናቱን ላባቱ ገዳይ ለጠላት የጦር አዛዥ ገጸ በረከት ያቀረበ ባንዳ በነጻነት ማግስት ሲሾም ሲሸለም ባንጻሩ ደግሞ አርበኛ ወንድሙ በጦር ተከቦ ሲገደል ማየት እጅግ አድርጎ ይጎፈንናል፡፡ ዛሬ በሃገራችን የምናስተዉለዉ ተጨባጭ ሁኔታም ይህንን ሀቅ ነዉ ፡፡ እነዚህን ሁሉ በመጽሃፉ ዉስጥ ተብራርተዉ ተዘርዝረዉ ያገኙዋቸዋል፡፡ ‹‹ሱዳኖች ከኢትዮጵያ የመሬት ጥያቄ ኖሯቸዉ ሳይሆን ሕወሃት ፋኖ በነበረበት ወቅት ምሽግ በመሆን ሁለንተናዊ አገልግሎት ስለ ሰጡት ያንን ዉለታ ለመመለስ ነዉ ሲሉ የራሳቸዉን ግምት ያስቀምጣሉ፡፡ሌሎች ወገኖች ደግሞ ‹የለም ህወሃት የመተማመን የጠረፍ ወረዳዎች በድፍረት እየቆረሰ ለሱዳኖች ለመስጠት ያቀደበት ምክንያት የኋላ ኋላ ኢትዮጵያን መግዛት ቢሳነዉ ትግራይን ገንጥሎ የትግራይ ሪፐብሊክ የሚሉትን ሲመሰርት ዝቅ ሲል የጎንደር ህዝብ ከፍ ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ ሴቲት ሁመራንና ወልቃይት ጠገዴን አብሬ አላስገነጥልም ብሎ ጦር ቢሰብቅ የሱዳንን አጋርነት ስላመነበት አስቀድሞ የጦር ቃል ኪዳን ስንቅ ማስቀመጡ ነዉ ›› በማለት ስጋታቸዉን ይገልጻሉ። ፡፡ ከመሐኃፉ ተወሰደ

0.0 (0 reviews)