አመራር እና ተጠያቂነት

አመራር እና ተጠያቂነት

Author/s: አለሙ አማረ

Subjects

Management, Non Fiction, Self Development

Published Year

2011 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

በአንድ አገር ውስጥ የሚከናውኑ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ ሁኔታዊች ዜጎችን ሁሉ መንካታቸው አይቀሬ ነው። ዜጎች ለዚህ ክስተት በግልና በቡድን ሆነው የሚሰጡት ስልታዊ ምላሽም የዜግነት ግዴታቸው ነው። ይህ መጽሐፍ ተጠያቂነትን በተመለከተ አውደ ሰፊ ንድፈ ሀሳቦችን በማንሳት ማንሸራሸር ተቀዳሚ ዓላማው ባይሆንም ከአመራርና ከተጠያቂነት አንጻር ዓለም አቀፋዊ አስተሳሰቦችን የሚያንጸባርቁ አተያዮችና ንድፈ ሃሳቦች ተካተዋል። የመጽሐፉ አብይ ትኩረትም እነዚህ ንድፈ ሀሳቦች አሁን ባለው የአገራችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ መንፈሳዊና ማህበራዊ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት ሊተገበሩ እንደሚችሉ ማሳየት ነው። በአጠቃላይ በዚህች አገር በየትኛውም ዘርፍ ላይ የሚስተዋለው ግርታና የግጭት መንስኤ ተጠያቂነትን መሸከም የሚችል ትከሻ ያላቸው መሪዎች ከመጥፋታቸው የመነጨ ነው። ይህ መሰረታዊ ችግር እንደሆነ ካመንን መሰረታዊ መፍትሔው ደግሞ በየትኛውም የአመራር ደረጃ ላይ የሚገኙ መሪዎችን ብቻ ሳይሆን ማህበረሰቡ ጭምር የሚጋራውን የተጠያቂነት ባህል ማጎልበትና መተግበር ነው።

0.0 (0 reviews)