ተንከተም

ተንከተም

Author/s: ስምዐኮነ መልአክ (ሊቀ ሊቃውንት)

Subjects

Non Fiction, Religious, History, Self development

Published Year

2014 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ሃይማኖታቸውን በቅኔ፣ ኑሯቸውን በምናኔ ሲገልጹ ኖረዋል። በገዳም፣ በጉባኤ ከሚገኝ መምህር እና ደቀ መዝሙር ጀምሮ በቤተ መንግሥት እስከሚኖር ንጉሠ ነገሥት ድረስ ባለቅኔዎች ይበዙበት ነበር። ሃይማኖቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው፥ ራሱን ለእግዚአብሔር ሰጥቶ፥ ራሱን ክዶ በመኖር ሃይማኖቱን ይገልጸዋል። በሥጋ ሆኖ ከሰማያውያን መላእክት ጋራ የተካከለ፣ የተመሳሰለ ሕይወትን ከኖረ፥ እርሱ በእውነት ሃይማኖቱን ጠንቅቆ ዐውቋል ማለት ነው። ሃይማኖት፥ ከእግዚአብሔር ጋራ የሚያገናኝ ድልድይ ከመሆኑም ባሻገር የታሪክ፣ የጥበብ፣ የባህልም ምንጭ ነው። ሃይማኖት በሌለው ሕዝብ ዘንድ ጥበብን፣ ባህልን፣ ታሪክን ማግኘት ያስቸግራል። በዓለም ላይ የአይሁድን ያህል ዓለምን የለወጠ ጥበብ፣ ታሪክና ባህል ያለው ሕዝብ ያለ አይመስለኝም። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ አይሁድ ሃይማኖት ስለነበራቸው ነው። ይህ መጽሐፍም መነሻ ያደረገው፥ መሠረተ ሃይማኖት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን ሲሆን፣ አቀራረቡም በሁለት ዐበይት ክፍሎች ተከፍሏል። የመጀመሪያው ክፍል፦ በሀገራችንም ሆነ በሌላው ዓለም የሚስተዋለውን አጠቃላይ የነገረ ሃይማኖት ጉዳይ የሚዳሥሥ ሲሆን፣ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ፦ "ነአምን በአሐዱ አምላክ" ከሚለው አንቀጽ ጀምሮ "ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን" እስከሚለው ድረስ ያለውን የጸሎተ ሃይማኖትን ቀኖና ያብራራል። አከፋፈሉም፦ የአባቶቻችን አስተምህሮ የተከተለ ነው። ሁለቱ ዐበይት ክፍሎች፦ የሁለቱ ኪዳናት፣ ዐሥራ ሁለቱ አናቅጽ ደግሞ ሁለቱን ኪዳናት የፈጸመ የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ምሳሌዎች ናቸው። በአጠቃላይ ከአባቶቼ የሰማሁትን፣ በጉባኤ የተማርሁትን የቤተ ክርስቲያናችንን መሠረታዊ ትምህርት ለደቀ መዛሙርት እና ለምእመናንም ይጠቅም ዘንድ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው፡፡

0.0 (0 reviews)