ባዲገዝ
Summary
"ባዲገዝ" የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በተለይም እንደ ሀገር ያለንበትን ወቅታዊ ስንጥቅ በደንብ የሚፈትሹ፣ የሚያስገነዝቡ፣ ከእንቅልፋችን እንድንነቃ ጆሯችን ላይ የሚያቃጭሉ እና የሚሄሱ ወጎች ተቀምረዋል፡፡ ደራሲው ከሀገር በቀል እውቀት ልምዱ የቀሰማቸውን እንቁ የልጅነት ፍልቅልቅ ትውስታዎች ከዛሬው እኛነታችን ጋር እያጋመደ ሀገራዊ ተብሰልስሎትን፣ ማህበራዊ መስተጋብርን፣ ሰውነትን (ኢትዮጵያዊ እሴትን)፣ ኪነ-ጥበብን፣ ማህበረ-ፖለቲካን፣ በትዝብት መንቆር እየነቀሰ ያስኮመኩመናል፡፡ ነግና ሰርክ የሚኮረኩሩን፣ እንደ አልባሌ በጎንዮሽ የምናልፋቸው፣ ውስጥ ውስጡን የሚከነክኑንን ርዕሰ-ነገሮች በማንጠር በንስራዊ እይታው በብዕሩ እየገለበ ድጋሜ እንድናጤናቸው ብሎም እንድንደመምባቸው ጭምር ይጋብዘናል፡፡