ኑሮ ከወላይታው አበላ ጫካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ

ኑሮ ከወላይታው አበላ ጫካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ አሜሪካ

Author/s: ዳዊት አላምቦ

Subjects

History, Non-Fiction

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

በወላይታ ዞን ጉኑኖ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነኝ፡፡ አቶ ዳዊትን ማወቅ የጀመርኩት በሶሻል ሚዲያ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት በሚያስተላልፋቸው ጽሑፎች በሬድዮና በቴሌቪዥን እየቀረበ ከፀረ ኢትዮጵያ ሀይሎች ጋር በሚያደርጋቸው ክርክሮች ነው፡፡ ከዚያም አግኝቼአቸው ለመተዋወቅ ፈልጌ በፌስቡክ አድራሻቸውንና ስልካቸውን ፈልጌ በማግኘት ደውዬ ተገናኘን፡፡ በመጀመሪያ ጊዜ ሳነጋግር እንደቅርብ ወንድም በጥሩ ስነምግባር አነጋገሩኝ፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚኖሩም ገለፁልኝ፡፡ እኔም ያለኝን አድናቆት ገልጬላቸው፣ ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት ተመሳሳይ አስተሳሰብ ስላለን በጋራ መስራት እንዳለብን ተወያየን፡፡ አቶ ዳዊት በተለይ ለተወለዱበት አካባቢ በጣም የሚቆረቆሩና መልካም የሚያስቡ መሆናቸውን የተረዳሁት እያንዳንዱ የአሜሪካ ነዋሪ በስራ ተወጥሮ ገቢ ለማግኘት በሚሯሯጥበት ሀገር የራሳቸውን ጥቅም በመተው በአሜሪካ የሚገኙትን ወላይታዎች በማሰባሰብ የወላይታ ተወላጆች ወዳጆች ማህበር (አዋና) የተባለውን ለመመስረት ሌሎች በጎ አሳቢ ወላይታዎችን በመቀስቀስ፣ ቁጭ ብሎ የስልክ ቁጥራቸውን በመፈለግና በመደወል፣ ግንኙነት በመፍጠር የድርጅቱን መሰረት የጣሉ ሌትና ቀን የሰሩ ሰው ናቸው፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተ በኋላም የስራ አስፈፃሚ ሆነው በርካታ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ አቶ ዳዊት የወላይታ ማህበረሰብ ከአካባቢው አጎራባች ህዝቦች ጋር በፍቅርና በሰላም እንዲኖር የኢትዮጵያ ተምሳሌት የሆነ በጋራ የአስተዳደር መዋቅር እንዲኖረው ባላቸው አቋም በወቅቱ የተሳሳተ መንገድ በሚከተሉ ግለሰቦች ውግዘት ሲደርሳባቸው ነበር፡፡ በተለይ ከአሜሪካ ወደ ሀገር መጥተው የወላይታ ህዝብን በየወረዳ ተዘዋውረው ለማስተማር አቅደው በራሳቸው ሙሉ ወጪ ሲንቀሳቀሱ እኔም ሂደቱን ለመደገፍ ከእሳቸው ጋር ስንቀሳቀስ የተመለከትኩት በየመድረኩ ስለ እውነት፣ ስለ ሰላም፣ ስለ አብሮነት፣ ስለፍትህና የጋራ ተጠቃሚነት ሲያስተምሩ ነበር፡፡ በተለይ በውጭ ሀገር በኖሩባቸው ጊዜያት ያገኙትን ልምድ ሲያካፍሉ ህዝቡ በከፍተኛ ደስታ መልዕክታቸውን ሲከታተል ዐይቻለሁ፡፡ ከዚያም ባሻገር የአካባቢው ወጣቶች ከአመፅና ከሽብር ተግባር በመቆጠብ ሃሳባቸውንና ፍላጎታቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈፅሙ ሲናገሩ ነበር፡፡ አቶ ዳዊት በውጭ ሀገር ኢትዮጵያን ለማጠልሸት የሚነዛውን ዉሸትና የጥላቻ ዜና ለመቋቋም የተለያዩ ሰልፎችን በማስተባበርና በመምራት መቆየታቸውን በኢቲቪና በሌሎች ሚዲያዎች ተመልክቻለሁ፡፡ አቶ ዳዊት ለሀገራቸው ባለው ያልተቋረጠ በጎ አሳቢነት ትውልድ እንዲማርበት የሕይወት ታሪካቸውንና ስለ ውጭ ህይወታቸው ልምድ ያካፈሉበትን ተነቦ የማይጠገብ መጽሐፍ ለማንበብ በመብቃቴ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራም ሆነ በሀገር ውስጥ ነዋሪ ዜጋ የእሳቸውን ፈለግ በመከተል በፅናት ለሀገሩ እንዲቆም አሳስባለሁ፡፡

0.0 (0 reviews)