የቴዲ አፍሮ የታላቅነት ምስጢር
Summary
መኖር የሁሉም ነገር መነሻ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ያለው በመኖር ውስጥ ነው፡፡ በመኖር ውስጥ በህይወት ለመኖር ወይም የተሻለ ለመኖር ከሚደረገው ትግል ቀጥሎ የዓለምን ገሀድ እና ምስጢር ማየት፤መስማት፤ መቅመስ፤ ማሽተት እና መዳሰስ ይቻላል፡፡ በእነዚህ ስሜቶቻችን ዓለምን እናውቃለን፡፡ ዓለምን ከስሜት ከፍ ብሎ፤ ከማወቅ በተሻለ ፤ በልዩ ተሰጥኦ ቀድሞ የተረዳ ደግሞ ላልተረዳ ለማስረዳት ሲል ጥበብን ፈጥሮና መርጦ የሰው ልጅ ከዘፍጥረት ሀ፣ሁ ጀምሮ አያሌ የጥበብ አሻራዎችን አስቀምጧል፡፡ ከፅህፈት ታሪክ በኋላም ስነ-ፅሁፍ የዓለምን ሁለንተና ለመግለፅ ትልቁን ድርሻ ይዞ ይገኛል፡፡የቴዲ አፍሮ የታላቅነት ምስጢር የተሰኘው መፅሐፍ ስለዝነኛው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ጅማሬ እስከ ደረሰበት የተወዳጅነት ጥግ ለዛ ባለው አቀራረብ በጥሩ ቋንቋ ተከሽኖ ቀርቧል።