የነፍሴ ጥያቄ
Summary
ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር ጉባኤ ቤት ኮሚቴ አስተባባሪነት ነው፡፡ ኮሚቴው የተቋቋመው በብፁዕ አቡነ አብርሃም መልካም ፈቃድ ጉባኤ ቤቱን በሁለንተናዊ አገልግሎቱ ድጋፍ እንዲያደርግ ታስቦ መሆኑ የታወቀ ሲሆን እስካሁን የጉባኤ ቤቱ ቋሚ መቀመጫ ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው የፈለገ ግዮን አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንድነት ገዳም መብራት፣ ውኃ፣ መንገድ እና ሌሎችም ያልተሟሉለት በመሆኑና ለደቀ መዛሙርቱ አኗኗር የማይመች በመሆኑ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር በማሟላት ላይ ይገኛል፡፡ ይህም መጽሐፍ ለዚህ አገልግሎት ማሟያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ መጽሐፍ የሚገዛ ማንኛውም ሰው መጽሐፉን በማንበብ ከሚያገኘው ጥቅም በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያናችን አንድ ትልቅ የምስክር ጉባኤ ቤት እንዲኖራት ከሚሠሩ ትጉኃን አገልጋዮች ጎን የተሰለፈ መሆኑን መናገር እንፈልጋለን፡፡ ጉባኤ ቤቱ በቀጣይ የሚሠራቸው በከፊል • የመጻሕፍትን ምሥጢር የጠገቡ ዐይናማ ሊቃውንት የሚወጡበት • ዘመኑን የዋጁ ሰባክያነ ወንጌል ማፍራት • በተለያዩ ዘመናት የተነሡ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ያጣመሟቸውን ታሪኮች፣ መጻሕፍት፣ ባህለ ሃይማኖት ወዘተ የሚያጠና የምርምር ማዕከል ማቋቋም • ለሕፃናትና ለዘመናዊ ትምህርት ተማሪዎች ሀገራዊውንና ሃይማኖታዊውን ዕውቀት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ከምንሠራቸው መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡