በታዳጊ ኢኮኖሚ
Summary
ይህ አንተ ስለ ንግድና ምጣኔ ሃብት አዘጋገብ ማወቅ የምትፈልገውን ሁሉ ያካተተ አጠቃላይ መጽሐፍ አይደለም። ሥራ እንደሚበዛበት አንድ ጋዜጠኛ ስንት የሰብሰብኳቸው ጠቃሚ መፅሐፎች አቧራ እንደወረሳቸው፣ ላነባቸው እያሰብኩ በጊዜ ማጣት ብቻ ሳላነባቸው የቀሩ እንዳሉ አውቃለሁ። ይቺ አነስተኛ መፅሐፍ ግን ወድያውኑ የንግድና ምጣኔ ሀብት ትረካህን ለማሻሻል የተቀየሱ አስር ምክሮችን ትሰጥሀለች። መፅሐፍዋ በንግድ ጋዜጣ ላይ በመላው ዓለም የሚያጋጥሙ አንዳንድ ቀላል፤ አንዳንድ ደግሞ መሠረታዊ የሆኑ ችግሮችን ትፈታለች። በነኚህ ችግሮች ላይ ያተኮርኩበት ምክንያት በተደጋጋሚ የሚታዩና በቀላሉ መፍትሄ ሊገኝላቸው የሚችሉ ስለሆኑ ነው። ከነኚህ ምክሮች አንዱን ወይም ሁለቱን ብትከተል አንባቢዎችህ በፅሁፍህ ላይ ያለውን ልዩነት ይገነዘባሉ፡፡ ምንም እንኳን ለአመቺነት ይህች መፅሐፍ (booklet) የጋዜጣ የንግድ ዘጋቢዎችን በብዛት ብትጠቅስም ያንኑ ያህል ለብሮድካስት ጋዜጠኝነትም ምክሮቿ ጠቃሚ ናቸው፤ ከንግድ ሌላ ለሌሎችም አዘጋገቦች በሥራ ላይ ይውላሉ።