ቤልጀጴራ

ቤልጀጴራ

Author/s: አበበ ፈንቴ ገላዉ

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

2014 አ.ም

Book Type

Audio

Summary

በዚህ ልብወለድ መጽሐፍ ውስጥ የፈጠርኋቸው ገጸ ባሕርያት በተለያዩ ጊዜያት ውስጥ የሚፈጠሩ ክስተቶችን እያነሱ አንዳንዴም የክስተቶች አካል በመሆን የሚሞግቱና የመፍትሔ ሐሳብ እያቀረቡ በራሳቸውና ባመኑበት መንገድ የሚነጉዱ ናቸው፡፡ እንዲሁም ያልገባቸውን ነገር ከመጠየቅ ወደ ኋላ የማይሉና ለዓላማቸው መሳካት ሲሉ አስፈሪና ሊደፈሩ የማይችሉ ነገሮችን ጭምር በድፍረት ሲሞክሩ ይታያሉ፡፡ በተጨማሪም ለሰው ልጆች ኹሉ እኩል ፍቅርና አክብሮት ያላቸው፤ በየእምነታቸው ፈጣሪያቸውን የሚፈሩና ሥነ-ምግባርን የተላበሱ፤ ለሀገራቸው ሰላምና እድገት ሲሉ ቀን ከሌሊት የሚታትሩ፤ የርእስ በርእስ ግጭቶችን በማጥበብ በአንድነትና በፍቅር የምንኖርባትን ታላቅ ሀገር ለመገንባት የልብ መሻት ያላቸው፤ እንዲሁም የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማየት ጉጉት ያደረባቸው ሆነው ይታያሉ፡፡ ይህን መጽሐፍ በዚህ መንገድ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ትልቁና ዋናው ነገር በእኔ ትውልድ ላይ የሚታየውን ዘርፈ ብዙ ግድፈቶችንና ክፍተቶችን ቢያንስ አንዱን እንኳን እሞላ ዘንድ በማሰብ ነው፡፡

5.0 (1 reviews)