ከማዕዘኑ ወዲህ
Summary
ከዚህ መጽሀፍ ሁለት ነገሮችን አግኝቼበታለሁ፡፡ ጽናትና ይቅርታ! የሕይወት ቁልፍ ዕውቀት የሚባለው የፈተናን ጥቅምና ጣዕም በቅጡ መረዳት ነው፡፡ ለምሳሌ ከክረምት ይልቅ በጋ ደስ ቢልም ሁሌ በጋ ቢሆን ግን ይሰለቻል፡፡ ልክ እንደዚያው መከራም የሕይወት ውበት ማሳያ ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገር የገጠመንን ፈተና ሳያጋንኑ በጸጋ ተቀብሎ ወደ ፊት ለመጓዝ መጣር ነው፡፡ ከዚህ መጽሀፍ ይህንን ጥንካሬ አግኝቼበታለሁ፡፡ ይቅርታን በተመለከተ መጽሀፍ ቅዱስ ራሱ የይቅርታ ውጤት ነው፡፡ ይቅርታ ሰዎች በድጋሚ እንዲኖሩ የሚሰጣቸው ዕድል ነው፡፡ ይቅርታ የሰው ልብ የሚታከምበት ቁልፍ መድኃኒትም ነው፡፡ ሰዎች ውበታቸውን ለመጠበቅ ወጪ እንደሚያወጡት ሁሉ የልባቸው ውበትና ጤንነት ይጠበቅ ዘንድ ይቅርታ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህንን ሀቅ በዚህ መጽሀፍ ውስጥ አግኝቻለሁ፡፡ የመጽሀፉ ጸሀፊ ያን ያክል ግፍና በደል ተፈጽሞበት ያን ሁሉ ቂምና ጥላቻ ትቶ ይቅርታ ማድረጉ በእጅጉ እንዳደንቀውና እንድማርበት አድርጎኛል፡፡ አካሉ ዊልቸር ላይ ተቀምጦ እጆቹ ብዕር መጨበጥ ባይችሉም አዕምሮው ግን በይቅርታ ነጻ ወጥቶ እጅግ ርቆ እየተጓዘ ነው፡፡ የጽናትም ተምሣሌት ነው፡፡ መጽሀፉን ሁሉም ሰው እንዲያነበው እጋብዛለሁ፡፡ ዳግማዊም ደጋግመህ እንድትጽፍ አደራ እላለሁ፡፡