ሐዋዝ

ሐዋዝ

Author/s: ከፈለኝ ዘለለው

Subjects

Ficition, Self Development, Philosophy, Communication

Published Year

2014 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

"ሐዋዝ" የግዕዝ ቃል ሲሆን በትርጓሜውም "የሚያምር" ፣ "ደስ የሚል" ፣ "መልካም" እና "ቆንጆ" ሲል ይፈታዋል፡፡ ይህን ውብ ቃል የመፅሐፌ ርዕስ አድርጌ የተጠቀምኩበት አንኳር ምክንያት መፅሐፌ ውስጥ ያኖርኳቸው ሀሳቦች ደስ የሚሉና መልካሞች አንደሆኑ አምኜ ነው፡፡ ረብ - ባጡ እይታዎች የታገተን አዕምሮን ቀያሪና ፤ ፋይዳ የለሽ አስተሳሰቦችንም ቅርፅ ሰጪ መፅሐፍ ነው በሚል እምነት "ሐዋዝ"ን የመፅሐፌ ርዕስ አደረኩት፡፡ "ሐዋዝ" አዕምሮን ለማበልፀግ በ 2014 ዓ.ም ያሳተምት ዝንፈተ - ሕይወትን መግሪያ መፅሐፍ ነው፡፡ የአማራኛ ቋንቋችንን ጥልቀት በመልከ - እልፍ ሀሳቦች ውስጥ በማዋቀር ላስተላልፍ የሻትኩትን ጭብጥ ባልተለመደ አቅጣጫ ለማቅረብ የሞከርኩበት አራተኛ መፅሐፌ ነው፡፡ የመፅሐፌ ዋና ተልዕኮና አጠቃላይ ጭብጥ የሰው ልጅን የአኗኗር ዘይቤ በበጎ መግራት ፤ በምድራችን ላይ ተንሰራፍተው የሚስተዋሉ የአስተሳሰብ መንጋደዶችን ሰውኛ ቅርፅ መስጠት ፤ የሰው ልጅ በኑሮው ለሚገጥሙት እክሎች እጅ ባለመስጠት በብርታትና ፅናት ታግሎ ራሱን ለአሸናፊነት እንዲያበቃ ማነሳሳት ነው፡፡ በመፅሐፌ ውስጥ ሳቢ ገጠመኞችን ምሳሌ አድርጌ ፤ ማራኪ የቋንቋ አጠቃቀምና ስብጥሮችን ለጭብጦቼ ማጉሊያነት ተጠቅሜ ፤ ኢትዮጵያዊ ለዛና ወግን በተላበሱ የቃላት ክሸና ፤ ለውጥን ለተራቡ ነፍሶች እንደምግብ የሚጣፍጡ መልዕክቶችን በእንጎቻነት አቅርቤአለሁ፡፡ የእኛው የሆኑ ቱባ ፅሁፋዊ ሀብቶቻችንን የእኛው በሆኑ ጨዋ ስነ - ፅሁፋዊ ፍሰቶች ለእኛው የጥበብ ጥማተኞች ለማጋራት ጥረት ያደረኩበት ግብረ - ገብነት ላይ ያተኮረ መፅሐፍ ነው፡፡

5.0 (2 reviews)