ጠርዝ ላይ
Summary
መጽሀፉ አራት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እነዚህም የየዘመኑን የኢትዮጵያ መልክ፣ የቋንቋ እቅድና ምርጫ፣ ጋዜጠኝነትና ማህበረሰባዊ የስነምግባር ይዞታችን ናቸው፡፡ የአቀራረብ ቅርጻቸው ዲቃላ ነው፤ አልፎ አልፎ ከኑሯችን እንዳይርቁ፣ ለአንባቢ እንዳይጎረብጡ ከወግ ተውሰዋል፤ ግባቸውን ይመቱ ዘንድ ደግሞ አልፎ አልፎ በየመስኩ ያሉ ድርሳናትን ተንተርሰዋል፡፡ የወግና የጥናታዊ ጽሁፍ ድቅል ናቸው፤ መራር ወግ ልንላቸው እንችላለን፡፡