የሕይወት ቀለማት

የሕይወት ቀለማት

Author/s: ጥበቡ ተፈራ

Subjects

Biography, Non Fiction

Published Year

2013 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

የህይወት ቀለማት መጽሀፍ እንደስያሜው ህይወት ብዙ አይነት እና ዝብርቅርቅ መሆኗን ያሳየናል፡፡መጽሀፉ በስምንት ምዕራፎች ተከፋፍሎ የተሰናዳ ሲሆን በርካታ የህይወት ገጠመኞችን እና ውጣውረዶችን እያዋዛ ያስነብባል፡፡አንድ ወደ አለማችን ከመጣ 60 አመታትን ያልዘለለ ጎልማሳ ታሪክ ቢሆንም አንዳንድ ጊዜ የዚህን እድሜ እጥፍ በዚች ምድር ላይ ኖረው ይህን ሁሉ ውጣውረድ የሚያሳልፉ ሰዎች ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡የመጽሀፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሚያስነብበው ፀሀፊው በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን በሚባለው አካባቢ ስላሳለፈው የልጅነት ትውስታዎቹ ሲሆን፣ በደርግ የመጀመሪያዎቹ ያገዛዝ ዘመን ወጣቱ ከወታደራዊው መንግስት ጋር ያደርግ የነበረውን ግብግብ እና ገጠመኞቹን ያጫውተናል፡፡በዚሁ ምዕራፍ የሀገራችን እውቁ ሙዚቀኛ የመጀመሪያው ፒያኒስት እና የራስ ባንድ መስራቹ አጎቱ ተፈራ መኮንን ያልተሰሙ ነገሮችን ያሰማናል፡፡በቀጣዩ ምዕራፍም ኢትዮጵያ ስለነበራት ጠንካራ የባህር ኃይል እና ስለ ዝነኛው የባህር ኃይል የሙዚቃ ክፍል ታሪክ፣ደራሲው በአስመራ ቆይታው ያሳለፋቸውን ጊዜያት ፣ በተለይ በ1974 ዓ.ም የኤርትራን ችግር ለመፍታት ተሞክሮ ስለነበረው የቀይ ኮከብ ዘመቻ እንቅስቃሴ ይዳስሳል፡፡በቀጣዮቹ ምዕራፎችም በምዕራብ ኢትዮጵያ አሶሳ እና ወለጋ ስላሳለፈው ሰፊ የህይወት ተሞክሮ በተለይ ጊዜው የመንግስት ሽግግር የሚደረግበት ወቅት ስለነበር በጦርነት እና በግርግር ያለፉ መራራ ጊዜያትን ያስቃኘናል፡፡ደራሲው ያለፈበትን የገጠር መምህርነት ህይወቱ፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ገጠመኞቹ፣የአሶሳ እና አካባቢውን የተፈጥሮ በረከቶች እና የሰፈራ መንደሮችን ትዝታ ያስቃኘናል፡፡በቀጣይ ምዕራፎችም የቤተሰቡን እና የልጅ አስተዳደግ ተሞክሮዎቹን፣የማህበራዊ ህይወቱን፣የጉዞ ማስታወሻዎችን፣የከፍተኛ ትምህርት ገጠመኙን ከዳሰሰ በኋላ ለሀገሩ መልካሙን ተመኝቶ መፅሀፉን ያጠቃልላል፡፡ በጥቅሉ ደራሲው በኤርትራ ወለጋ እና አሶሳ ተዟዙሮ አዲስ አበባ ላይ ስለከተመው ህይወቱ ሲሆን ለወጣቱ ትውልድም ትልቅ ስጦታ እንደሆነ ይታመናል፡፡መፅሀፉ ችግርን በብልኃት እና በዘዴ እንዴት ማለፍ እንደሚቻል ትምህርት ይቀሰምበታል፣ሁሉም ሰው ይህን ፈለግ ተከትሎ የህይወት አሻራውን አስቀምጦ ቢያልፍ ለቀጣዩ ትውልድ መልካም እርሾ ሆኖ እንደሚያገለግልም ይገፋፋል፣ ያነሳሳል፣ያበረታታል፡፡

5.0 (1 reviews)