በመንገዴ ላይ
Summary
"በመንገዴ ላይ" የተሰኘው መጽሐፉ ደራሲው ከልጅነት እስከ ዕውቀት ዕድሜው ያለፈባቸውን የሕይወት ውጣ ውረዶች፤ ኢትዮጵዊ አኗኗራችንን፤ እውነተኛ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን በሚገርም የቋንቋ ለዛ፤ የታሪክ ቅደም ተከተል፤ በልዩ የአተራረክ ስልት አቅርቦልናል፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ የቀረቡት ታሪኮች ከቃላት አገባብ ጀምሮ የገጠሩንም የከተማውንም ሕይወት፤ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር የአነጋገር ዘይቤውን፤ ቅኔውንና ምሳሌያዊ አነጋገሩን ሳይቀር እየመዘዘ ሁላችንም ያደግንበትን፤ ያለፍንበትን መንገድ ዱካውን የኋሊት ተጉዘን በምናብ እንድናስታውስ "በመንገዴ ላይ" ሲል አብጠርጥሮ እያበራየ አጋርቶናል፡፡ መጽሐፉ ኢትዮጵያ ተነግረው በማያልቁ፤ ተተርከው በማይጠገቡ እጅግ ውብ ገጾች ያሸበረቀች የድንቅ ባለታሪክ ሕዝቦች ሀገር መሆኗን ፍንትው አድርጎ አሳይቶናል፡፡