ምስካበ ጾታ
Summary
ይህ መጽሐፍ አምስት ክፍሎች ሲኖሩት በእያንዳንዱ ክፍል የሚነሱ አንኳር ጉዳዮች በስፋትና በጥልቀት ቀርበዋል፡፡ የመጽሐፉ መድረሻ ቅዱስ ጋብቻ ሆኖ ከሥነ ጾታ ማለትም ወንድነትና ሴትነትን ከመተንተን ይጀምራል፡፡ ጠቅለል ባለ በልኩ የመጽሐፉ ይዘት ሲቀመጥ፦ በክፍል አንድ፦ ኦርቶዶክሳዊው የጾታ ትምህርት ጾታ ማለት ምን ማለት ነው? ከሚለው ጀምሮ በግልጽ የቀረበ ሲሆን አስፈላጊነቱም በሚገባ ተቀምጧል፡፡ በክፍል ሁለት፦ በጾታ ትምህርት ውስጥ የሚተኮርባቸው ጉዳዮች ዋና ዋና ጉዳዮች ተለይተውና ዘርዘር ባለ መልኩ ቀርበዋል፡፡ በክፍል ሦስት፦ ከጋብቻ በፊት የሚከወነውን እጮኝነት አስመልክቶ ቅድመ እጮኝነትና ጊዜ እጮኝነት ያለው ጊዜና ሊደረግ የሚገባውና የሚከለከለው ጉዳይ ሁሉ በሚገባ ተቀምጧል፡፡ በክፍል አራት፦ ፊትለፊት የሚታወቁት የጋብቻ ዓይነቶች ተጠቅሰው ኦርቶዶክሳዊው ጋብቻ ምን እንደሚመስልና አስፈላጊነቱ ጭምር መዝርዝር ቀርቧል፡፡ በክፍል አምስት፦ በዚህ ክፍል የመጽሐፉ ዋና መዳረሻ ለሆነው ቅዱሱ ክርስቲያናዊ ጋብቻ ለመብቃት የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ጉዳዮች ተመርጠውና ተለቅመው ቀርበዋል፡፡ ክፍል ስድስት፦ ይህ ክፍል ፈቃደ እግዚአብሔር ምንድነው? ብሎ ይጠይቅና የፈቃደ እግዚአብሔርን ምንነት ካብራራ በኋላ ፈቃደ እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚረዱንን ትክክለኛ መንገዶችንና ከፈቃደ እግዚአብሔር የሚያወጡንን የተሳሳቱ መንገዶች በንጽጽር ያቀርባል፡፡ ይህ ክፍል የመጨረሻው ክፍል እንደመሆኑ ማጠቃለያውንም ይዟል፡፡ መልካም ንባብ ከጥሩ ማስተዋል ጋር ይሁንልዎ