ደርሶ መልስ
Summary
‹ደርሶ መልስ› (በ2002 ዓ.ም የወጣ) ሄኖክ የተባለ ጊታሪስት ወጣት፣ በተለያዩ ጊዜያት አፍቅሯቸው ስለነበሩ አራት ፍቅረኞቹና ፍቅረኞቹ እሱ ስለእነሱ፣ እነሱ ስለእሱ ይሰማቸው የነበረ ጥልቅ ስሜት አዛንቆ የሚተርክ ሲሆን፣ ይህ ረጅም ልቦለድ የዚህን ዘመን የወጣቶችን ውስጣዊ መልክና ተብሰልስሎት በግልጽ ያሳየና በአተራረክ ቴክኒኩም አዲስነት የሚታይበት ስለመሆኑ የተመሰከረለት ነው፡፡ ቁጥራቸው ጥቂት በማይባሉ የሥነ ጽሑፍ ተመራማሪዎች ዘንድም ልቦለዱ ትኩረት የተሰጠውና ለሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ መመረቂያ ሥራነት የተመረጠ፣ ከእንዳለጌታ ተወዳጅ ልቦለዶች መካከል አንዱ ነው፡፡