የይቅርታ መስኮት
Summary
ይሄን መጽሐፍ እንድጀምር ያረጉኝ ሁለት አጋጣሚዎች አንድ ላይ ተከስተው ነው። በምኖርበት አሜሪካ ብዙ ግዜ አብረው የኖሩ አብረው ያደጉ፣ የተጋቡ፣ የወለዱ አለበለዚያም ከአንድ እናትና አባት ተወልደው እህትማማች፣ ወንድማማች የሆኑ ሰዎች፤ አብረው በፍቅር የኖሩበትን ዘመን እየረሱ፤ አይኑን እንዳላይ አይኗን እንዳላይ ሲባባሉ በተደጋጋሚ ስላየሁና፤ ከቀን ወደ ቀን ቁጥሩና ጉዳቱ እየጨመረ መምጣቱን በመረዳቴ ስለ ይቅርታ ለመጻፍ ወሰንኩ። ከየት እንደምጀምረው ሳሰላስል ደግሞ አንድ የሚገርም ጥቅስ አገኘሁ። <<እውነተኛ ይቅርታ ስለነበረን መልካም ግዜ ከልብ አመሰግናለሁ ማለት ስንችል ነው>> የሚል -ኦፕራ ዊንፍሪ የይቅርታ መስኮት የተወለደው ከነዚህ ነገሮች ነው። አብረን መጓዝ ባንችል እንኳን፤ አብረን የነበረንን ግዜ ደምስሰንና እረግጠን ለጥላቻ በር ከፍተን አንዳችን ሌላውን እያደማን በዚያ ከምንደሰት በይቅርታና በፍቅር እንታከም የሚል ጽንሰ ሐሳብ ይዟል።