የመኝታ ቤት ምስጢሮች

የመኝታ ቤት ምስጢሮች

Author/s: እንዳለጌታ ከበደ

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

ጥቅምት፣ 2011 ዓ.ም፡

Book Type

Ebook

Summary

"የመኝታ ቤት ምስጢሮች" (በ2002 ዓ.ም የወጣ) የአጫጭር ትረካዎች ስብስብ ሲሆን፣ ትረካዎቹ በኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚዳስሱ፣ በአብዛኛው በቤተሰብ ውስጥ በሚከሰቱ ሥነልቦናዊ ድቀትና ውድቀቶች ላይ ትኩረታቸውን ያሳረፉ ባለታሪኮች የተተረከበት ነው፡፡ የትረካዎቹም መቼት በከተማ ውስጥ ብቻ ሳይወሰን፣ እስከ ደቡብ ኦሞ ድረስ የዘለቀ ነው፡፡ ደራሲው እንዳለጌታ በትረካዎቹ የአባቶችን ጽናት፣ የእናቶችን ሕማም፣ የወጣቶችን ፍቅርና የልጆችን ተስፋ ለማሳየት ውብ ቋንቋ ተጠቅሞአል፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው መካከል ስለሚፈጥሩት አድልዎና ይህም በአስተዳደጋቸው ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ፣ በትዳር ላይ ስለሚፈጸም ውስልትናና ውስልትናው ስለሚፈጥረው ጫና በድህነት ሰበብ ስለሚደርስ ፈተናና በሌሎችም ቤተሰባዊ ጉዳዮች ላይ ያጠነጠነ ነው፡፡

5.0 (1 reviews)