የአማርኛ ሥርዐተ ጽሕፈት

የአማርኛ ሥርዐተ ጽሕፈት

Author/s: አብርሃም በዕውቀት ታረቀኝ

Subjects

Communication, Self Development, Non Fiction

Published Year

2014 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ይህ መጽሐፍ በሞክሼ ሆሄያት (ሀ፣ ሐ፣ ኀ፣ ሠ፣ ሰ፣ አ፣ ዐ፣ ጸ፣ ፀ) መካከል ያለዉን የአጠቃቀም ዝርክርክነት የሚያርም ነው፡፡ መጽሐፉ የተለያዩ ማጣቀሻዎችን መሠረት በማድረግ በሥርዐተ ነጥብ፣ በቃላት (ስሞች፣ ቅጽሎች …) ማብዛት ወቅት የሚያጋጥሙ ግድፈቶችን፣ በሙያ ቃላት ላይ የሚታየዉን ስሕተት፣ የምሕጻረ ቃላት አጠቃቀምና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የመጽሐፉ አዘጋጅ ጋዜጠኛ በመኾኑ በተለይ በመገናኛ ብዙኃን፣ በመማርያ መጻሕት፣ በፖለቲከኞች ንግግሮች … ላይ የሚስተዋሉ ሕፀፆችን ጭምር በግብዓትነት ወስዶ ነው መጽሐፉን ያዘጋጀው፡፡ ይህ መጽሐፍ አማርኛን ሥርዐተ ጽሕፈት ጠንቅቆ ለማወቅ ይረዳል፡፡ እስኪ የጀግናዉ አትሌታችን ስም በትክክል ሲጻፍ የቱን ይመስላል? “ሀይሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሃይሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሐይሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሓይሌ ገብረ ሥላሤ፣ ኀይሌ ገብረ ሥላሤ፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሤ፣ ኻይሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሀዪሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሃዪሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሐዪሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሓዪሌ ገብረ ሥላሤ፣ ኀዪሌ ገብረ ሥላሤ፣ ኃዪሌ ገብረ ሥላሤ፣ ኻዪሌ ገብረ ሥላሤ፣ ሀይሌ ገብረ ስላሤ፣ ሀይሌ ገብረ ስላሤ፣ ሐይሌ ገብረ ስላሤ፣ ሓይሌ ገብረ ስላሤ፣ ኀይሌ ገብረ ስላሤ፣ ኃይሌ ገብረ ስላሤ፣ ኻይሌ ገብረ ስላሤ፣ ሀዪሌ ገብረ ስላሤ፣ ሃዪሌ ገብረ ስላሤ፣ ሐዪሌ ገብረ ስላሤ፣ ሓዪሌ ገብረ ስላሤ፣ ኀዪሌ ገብረ ስላሤ፣ ኃዪሌ ገብረ ስላሤ፣ ኻዪሌ ገብረ ስላሤ፣ ሀይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ሃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ሐይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ሓይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ኻይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ሀዪሌ ገብረ ሥላሴ፣ ሃዪሌ ገብረ ሥላሴ፣ ሐዪሌ ገብረ ሥላሴ፣ ሓዪሌ ገብረ ሥላሴ፣ ኀዪሌ ገብረ ሥላሴ፣ ኃዪሌ ገብረ ሥላሴ፣ ኻዪሌ ገብረ ሥላሴ …” መልሱን ከመጽሐፉ ታገኛላችሁ!

0.0 (0 reviews)