ህይወት በዩኒቨርሲቲ

ህይወት በዩኒቨርሲቲ

Author/s: Dr. Tesfay Solomon Tsegay

Subjects

Self development, Management, Non Fiction

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

በዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ወይም ከዚያ በላይ ተማሪ ነህ? በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ስለተማሪ ህይወት የበለጠ መማርና ማወቅ ትፈልጊያለሽ? የትምህርት ጉዞህን ቀላልና የበለጠ አስደሳች ለማድረግ የሚያግዙህን ጠቃሚ ምክሮችንና ዘዴዎችን ማግኘት ትፈልጋለህ? ከእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ ለአንዱ አዎ ብለህ ከመለስክ፣ በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተማሪ ህይወት ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገውን ህይወት በዩኒቨርሲቲ የተሰኘውን መጽሐፍ መግዛት ያስፈልግሃል። ይህ መጽሃፍ ዋናውን የትምህርትና ሙያ ከመምረጥ ጀምሮ፣ መጠለያ ከማግኘት፣ ስለ ዶርም ኑሮ፣ ስለ ምግብ፣ ስለ ፋይናንስ ማስተዳደር፣ ክለቦችና ማህበረሰቦች መቀላቀል፣ ጓደኞች ማፍራት፣ ጭንቀትን ስለ መቋቋም፣ ስለ ፍቅር ግንኙነቶች፣ ስለ ጤና፣ ግጭትንና አለመግባባትን እንዴት ማስተናገድ እንደሚቻል፣ የአቻ ተጽእኖን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል፣ ጭንቀትንና ውጥረትን በአግባቡ ስለመያዝና ሌሎችንም የሚሸፍን ሁሉን አቀፍ መመሪያ ነው። በራሴ የተማሪነት ልምድና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከተለያዩ አስተዳደግና የትምህርት ዘርፎች የተውጣጡ ተማሪዎች የተደረጉ ጥናቶች መሰረት በማድረግ በተገኙ ግንዛቤዎች ላይ የተመሰረተ ነው። መጽሐፉ መረጃ ሰጪ ብቻ ሳይሆን አዝናኝና ማራኪም ነው። በቀልዶች፣ ጥቅሶችና ምሳሌዎች ተሞልቶ እንዲስቁና እንዲያስቡ የሚያደርግ ነው። ለመከታተልና ለመረዳት ቀላል በሆነ ግልጽና አጭር አረፍተ-ነገሮች ነው የተጻፈው። የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን በአግባቡ ለመጠቀም ለሚፈልጉ የመጀመሪያ አመትና ከዚያ በላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ተስማሚ ነው። ይህ በአይነቱ በሀገራችን የመጀመርያ የሆነውን በዩንቨርስቲ የተማሪ ህይወት ላይ ብቻ ያተኮረ መጽሃፍ ማንበብ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በትምህርትህና በወደፊት ህይወትህ ላይ የምታደርገው ምርጥ ኢንቨስትመንት ይሆናል።

0.0 (0 reviews)