የማለዳ ፍቅር

የማለዳ ፍቅር

Author/s: ዮናስ አብርሃም

Subjects

Non Fiction, Selfe Development, Short story, literature

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

"የማለዳ ፍቅር" 22 ጣፋጭ ታሪኮችን ይዟል። በሥነ-ምግባርና ሞራል ዕሴቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው። ምንጮቻቸው የተለያዩ ሃገራትና ህዝቦች ሲሆኑ፣ በመላ ዓለም ተሠራጭተዋል። አንዴ ተነበው የማይቀመጡ፣ በተደጋጋሚ ሊነበቡ የሚገባቸው ናቸው፡፡ በያዟቸው የኃሣብ ይዘትና ጥልቅ አሥተምህሮት። በዚህ መድብል ውስጥ የአንዳንዶቹ ታሪኮች ጭብጥ ለአንባብያን ዕንግዳ ላይሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ፍፁም አዲስነት ተላብሰዋል። ቁንፅል የሆኑት የሞራል ታሪኮች አድማሳቸው ሰፍቶ፣ የታሪኮቹ ሥፍራ ተገልፆ፣ ገፀ ባህርያት ተቀርፆላቸው፣ ፍሬ ነገራቸው ዳብሮ....የ "አጭር ልቦለድ" ቅርፅ ይዘዋል። በጋዜጠኛና ደራሲው 'ዮናስ አብርሃም' ምናብ ጎልብተው፣ በምሥል ከሣች ማራኪ ቋንቋ ተፅፈው በዓይነ ህሊና ይታያሉ -- ጣፍጠው ይነበባሉ። መደበኛ የንባብ ልምድ ካላቸው አንባብያን በተጨማሪ:- ማንበብ እየፈለጉ ከመፅሐፍ መቆራኘት ለተቸገሩና የንባብ ክህሎታቸውን ማሣደግ ለሚፈልጉ "ጀማሪ" አንባብያን ብርታት ይሠጣሉ። ለታዳጊ ልጆችም ተመራጭ ናቸው። የከፊሎቹ ታሪኮች ገፀ - ባህርያት ህፃናት ስለሆኑ ለሥሜታቸው ይቀርባሉ፤ ታላላቅ ዕሴቶችንና የህይወት ቁምነገሮችን ያስጨብጣሉ። በዚህ <የማለዳ ፍቅር> በተሰኘው የጣፋጭ ታሪኮች መድብል ራሳችንን እንድናይ፣ የሞራል አቋማችንን እንድንፈትሽ፣ ክፍተቶቻችንን እንድንሞላ፣ ሚዛናዊ ዕይታ እንድናዳብር....ወዘተ ያነቃቁናል።

3.0 (1 reviews)