ራስን ፍለጋ

ራስን ፍለጋ

Author/s: አዚዝ ሺፋ

Subjects

Non Fiction, Self development

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ራስን የማየት ጉድለታችን ሰፊ ነው። በሀሳብ እና በራስነታችን መካከል ያለውን ልዩነት መመልከቱን እናጎድላለን። የሀሳብ ክራችንን እየመዘንን ስለ ራስነታችን፡ ስለ ህይወት፡ ስለ ሁናቴዎች በብዙ መልክ እናጌጣለን። በመኖር አውድ ስንዘልቅ ለመስጠት የምንኖረው ያንኑ ነው። በራሳችን ሀሳብ የተጌጠ እኔነት ላይ ቆመን የእኔ የምንለውን ፍለጋ እንሮጣለን። በራሳችን ሀሳባዊ ክር የተሰፋ የህይወት መልክ ላይ ቆመን ስለ ህይወት ብዙ እንሆናለን። መኖር በራስ የተጌጠን ምናብ የመድረስ ትግላዊ ሜዳ ሆኗል። ያንን የህይወት እውነት ብለን መነሳት እንችላለን። ምክንያቱም ይበጀኛል ብለው ካሰቡት፡ የማሰብ ህልዉናዊ ምንነት ላይ ቆመው ቀድመው ከመተሩት፡ የእኔ፡ ለእኔ ብለው ከተቀበሉት ዉጭ መኖርን ማስቀጠያ መንገድ የለም። ችግሩ የመተሩትን ለመኖር የመትጋቱ ነገር ላይ ሳይሆን ለመመተር የቆሙበትን አቋቋም ማየት ያለመቻሉ ነው። በዚህ በብዙ እንጎድላለን። ሰርክ ራሳችንን የምንመዝነው የእኔ በሚል የተቀበልነውን በመቁረጡ መስፈሪያ እንጂ ያንን በመመተሩ ሂደት ባለ አቋቋም አይደለም። ከየት? ወደየት? እንዴት? ለምን? በሚለው ሳይሆን የተሰመረን በመቁረጡ ልኬት ነው ራሳችንን የምንፈልገው። በዚህም የእኔ የምንለውን ፍለጋ ሌላነትን መኖሩ ይበዛብናል። ራስነታችንን ከራሳችን ርቀን ነው የምንፈልገው። ራስነታችንን ከራሳችን ነጥለን የምንመለከተው። የእኔ የምንለውን የምንፈልገው ባልገባን ራስነታችን ላይ ቆመን ነው። ለራሳችንን የሆነን ነገር ለመስጠት እንተጋለን። ግና ራሱን አንመለከተውም። ተመለከትኩት በምንለው፡ የእኔ ብለን ከፊት በምናቀርበው እና ዉስጥ ባለው እውነታ መካከል ያለውን ልዩነት እና ተዛምዶ አንመለከተውም። የፈጠርነው የህይወት፡ የራስነት ሀሳባዊ ፈትል በምን ያክል ከራሳችን ርቆ እንደሠፈረ የምናስበው የለንም። መኖራችን ግን ያንን የመድረስ መሆንታን የምንኖርበት ነው። የመሆን ትጋታችንን ያልተመለከትነውን፡ አስተዉሎት ያልፈጠርንበትን የመድረስ አድርገን ከራስነታችን ርቀን እንሰፍራለን። ያ ከራስ መጠፋፋቱን አብዝቶብናል። ከራስ ጋር መጠፋፋት ከህይወት እውነት የመነጠል ነው። ከህይወት እውነት መነጠል መኖርን በተሳሳተው ለማድረግ ነው። መኖር በተሳሳተው ሲሆን ዉጤቱ በብዙ መጉደል ነው። እኔ፡ የእኔ በምንለው እና በራስነታችን፡ "ነው" በሚል በምንፈጥረው መልክ እና በእውነታው መሓከል ሁልግዜ ክፍተት(ልዩነት) እንዳለ ነው። መኖር መሆን የሚገባው እኔ፡ የእኔ የሚለውን ለማስቀጠል ሳይሆን ራስን ለመፈለግ ነው። "ነው" የሚሉትን ከማስቀጠል አድጎ በእውነታው ፍለጋ መሆን ጠቢብነት አለው። ያንን ለመድረስ በፍለጋ ተሳፋሪዎች ሆኖ መገኘቱን ይጠይቃል። በፍለጋ ሰረገላ በተሳፋሪነት ስትቆም ተቀብለህ የምታስቀጥለው ሳይሆን የምትጠይቀው፡ የምትፈትሸው ነው የሚበዛው። ያ ባንተ ዉስጥ አገኘሁት የምትለው ሀሳብ ሁሉ አንተ፡ ያንተ እንዳልሆነ የምትመለከትበት መንገድ ነው። በእኔነት የቆምንበትን ከማስቀጠል አፍታ ፈቅ ብለን የቆምንበትን እንመለክተው። ልማድ ላይ ቆሞ መልክ ፈጥሮ ከመነሳቱ አድገን በእውነታው ፍለጋ እንሁን። በአንድ ሚዛን አድርገን አሁናዊ አቋቋማችንን እንዳኘው።

0.0 (0 reviews)