ዛዝላ

ዛዝላ

Author/s: ወንድምየ ምክር

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

2004 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

የያዛትንም የ "ቆ" በትር ይዞ እየተጓዘ እያለ በቀድሞ ግሽ አባይ ምንጭ መነሻ በትሯ ተሰካች። ከሰማይም ቀሥተ ደመና ምልክት ታየ ፡ በአንዲት የቡሄ ምሽት ሰላምና ፍቅር በሚዘፈንባት ቀን ልጅነታችንን አጣምረን የወገናዊነት አንድነታችን ተቋልፎ የታች የላይ ሰፈር ልጆች ሳንባባል ሙልሙል ዳቦ ፍለጋ በዘመትንባት በዛች ጨረቃ ያለወትሮዋ ፈክታ በከዋክብት ሳይሆን በሚበሩት ችቦዎች ደምቃና ተውባ መንደርተኛውን በምናስደስትበት ቀን .ጥቅማችንን አሳልፈን ሰጥተን .ስለ እነሱ ጥቅም የምንተኛ ሁለት የተጣሉ የአሮጌውን ትውልድ ስሪቶች እነሱን ለማገላገል መሀላቸው ብንገባ አንድነታችን አልጣማቸውም። ቤተ መፅሐፍቶቻችን.የማንበቢያ ስፍራዎቻችን እንደሻሼ ታስረው ተቆልፈውባቸዋል። ባደረኩት ነገር ተፀፅቻለሁ መፀፀቴ ብቻውን ለህሊናዬ እረፍት አልሰጠውም ። “ብዙ ነገር እጃችን ላይ ነው ያለው።ግን እንዳናይ ዐይነ ልቦናችን ተሸፍኗል፡፡ አገር ቤትም እያለን እንደዛ ነው ፤ ያለንን ነገር ያለማየት አባዜ አለብን። አብረን ሆነን አብረን አንኖርም፡፡” ይገርመኛል ግማሽነታችን እየወደደን ሙሉነታችን እንዴት ይጠላናል፡፡

0.0 (0 reviews)