የዕርግብ እሾህ
Summary
የኔ ራሔል የያእቆብን ራሔል ታውቂያት ይሆን! አላውቃትም ማን ናት ራሔል? መገመት ይከብዳል ወይስ በቅጣት መስማቱ ይበጅሻል? እገምታለው ግን ቅጣቱን ምን ልታደርግብኝ አስበህ ነው? ምናልባት ጨረቃን አምጥተሽ እንድትሰጭኝ፤ ወይም ክንፍ አውጥተን እንደ ወፍ ተያይዘን የምንበርበትን አስማት ማምጣት፤ ይህ ካልሆነ በልብሽ ውስጥ ቀብረሽ ልታኖሪኝ ቃል መግባት። የኔ ጌታ ልብህ የልቤ ከተማ ንጉስ ከሆነ ቆየ እኮ! ንጉሥ ይወርዳል ንጉሥ ይሻራል፤ የከተማ ንጉሥ ሁኘ መውረድና መሻር አልፈልግም። እና ምን ይሻልሃል ፍቅር? ፍቅር ካቅም በላይ ሲሆን ይፈስሳል እንዴ? ልቡን ላፍታ በልቡ ዓይን ተመልከተው፤ አዎ ይፈስሣል አላት። ወላሂ ፍቅር ሕይወት አለው። እንዴት ማለት? ፍቅር በልብ ማሳ ተዘርቶ፤ በእያንዳንዱ አካል ላይ በደምና በአጥንት በቅሎ በሚወዱት ሰው እቅፍ ሆኖ በሙቀት የሚጎመራና ባፈቀሩት ሰው ሆድ ውስጥ አቅርበው የሚመገቡት ህያው የሆነ ጣፋጭ የሕይወት ምግብ ነው ............... ወፎቹ ባጠገቡ እየበረሩ አለፉ፤ ቀናባቸው ...ቁልቁል ምድሩን ተመለከተው፤ ናፈቅው... መብረር የናፈቃት ክንፏ እንደ ተሰበረ ወፍና መራመድ ፈልጎ ምድር እንደ ራቀው ሰው ሁኛለሁ። በቃ በነፃነት መብረር የማልችል የምድር ወፍ ነኝ እንደ ዘመኑ ቢሮክራሲ... አለ።