አልባስጥሮስ
Summary
በፍቅር ሁሉ ያምር ይሰምር፡፡ ፍቅር ያደማምጣል ያረዳዳል ፡፡ ያስማማል ፡፡ ድብቅነትን ያርቃል፡፡ ግልጽነትን ያላብሳል፡፡ ፍርሃትን ያስወግዳል መቀራረብን ያሰፍናል፡፡ የፍቅር ፍርያት ብዙ ናቸዉ፡፡ ከዚህ ዉጭ ያለዉ አሉታዊ ዉጤት አለዉ፡፡ ሂደቱንም አሉታዊ ተጽዕኖ ልንለዉ እንችላለን። እስቲ በህይወት ዘመንህ እልህ የተጋባህበትን ዘመን መለስ ብለህ አስታዉስ ወይም ገጠመኝህን በትዝታ ዓይን ለአፍታ መለስ ብለህ ተመልከተዉ፡፡እልህ ብዙ አስቂኝና አሳዛኝ ታሪክ ትቶልህ አላለፈ ይሆን ከፊታቸዉም በእልህ በርካታ ታሪክ ሊጻፍባቸዉ ዝግጁ የሆኑ ህጻናት አሉ፡፡ ይህም ህጻናቱ በዘመናቸዉ ያልሆነ ታሪክ እንዳያስመዘግቡ አሉታዊ ተጽዕኖን ማዉገዙ ተገቢ ነዉ፡፡ ሰዉን በሰዉነቱ የሚቀበል ሰዉ ቁጥር ዘዉትር እየተመናመነ ቢሄድም የዓለማችን በረከቶች የሆኑ ሰዎች ድግሞ አይጠፉም፡፡ የትዳር ክቡርነት ተግዳሮቶቹና መፍትሄዎቻቸዉ ከማስተማር ይልቅ ፍቺ ያለዉን ጌዜያዊ እፎይታና ጠቀሜታ በቀጥታም ሆነ ተቋማዊ በሚመስል ሁኔታ እየተሰራበት ነዉ፡፡ ኑሮ ሲሰምር አጨብጫቢዉ አሞጋሹ አድናቂዉ አጽዳቂዉ እጅግ ይበዛል፡፡ ኑሮዉ አንዳች ሳንካ ሲገጥመዉ ደግሞ ቀድሞ ለምስጋናዉና ለአድናቆቱ የቆመለት ሁሉ ከምስጋናዉና ከአድናቆቱ በተቃራኒ በመቆም ለማንኳሰስና ለመተቸት ብሎም ለመፍረድ አንደበቱ ይስላል፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ግን ከዚህ ለየት ያለ ነዉ፡፡ ለሰዉ መክበርና መዋረድ ጊዜና ሁኔታ አስተዋጽኦ የላቸዉም ፡፡ ትንሳኤ ከሞት መነሳት ወደ ህይወትም መሸጋገር ነዉ፡፡አዲስ ተስፋ ሰንቆ በአምላክ ፍጹም እምነት ከወደቁበት መነሳትም ነዉ፡፡ ይህም የተቆጨን እንደሆነ ነዉ፡፡ያለፈዉ ዘመን ይበቃል ማለትን ማወቅ፡፡