አሸንላፊ
Summary
ባለታሪኳ በፍቅር ስም ለበዛ ብዝበዛና ግፍ ብትጋለጥም የደረሰባትን የክህደት አጋጣሚ እጅግ ውብና ለዛ ባለው ቋንቋ ትተርክልናለች፡፡ ብዙዎች በይሉኝታና በሀፍረት ለማንም ሊነገሩት የማይፈቅዱትን ሸፋፍነው የሚያልፉትን እውነት ግልጥልጥ አድርጋ ታወጋናለች፡፡ የፅሐፊዋን ጉብዝናና ድፍረት በሚገባ እናይበታለን። ወደአረብ ሀገራት የሚደረገውን ህገ ወጥ ጉዞ አስመልክታ የግሏን ገጠመኝ "የዶዲ ማስታወሻ" ብላ ከዚህ ቀደም ለአንባቢያን አበርክታለች። በዚህ መፅሐፍ ሴት ልጅ ከሚደርስባት የልብ ስብራት በኋላም ቢሆን የራሷን ትንሳዔ በብርታት ራሷ መስራት እንደምትችል እንማራለን። ከዛም ባለፈ በሕይወቷ ደምቃ እና ተውባ ለመታየትም ሆነ በርትቶ ኑሮን ለማሸነፍ የግድ የወንድ ልጅ ፍቅርም ሆነ ድጋፍ እንደሚያሻት ማሳያ ተምሳሌት ናት እንድንል ያደርገናል። ወንዶቹም ሴቶችም የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ቢያነቡት እየተዝናኑ የሚማሩበት መፅሐፍ ነው።