ሎዛ ዘ-ጸአት

ሎዛ ዘ-ጸአት

Author/s: መርዕድ እስጢፋኖስ

Subjects

NonFiction, Biography

Published Year

2014 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

ይህን መጽሀፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ።የራሴ የስደት ተሞክሮ ሲሆን የስደትን አስከፊም ይሁን በጎ ገጽታ ያሳያል ብዬ አምናለሁ። የሎዛ ዘፀአት ስደትን እጣ ፈንታቸው እድርገው የመረጡ የተሻለ ህይወት ፍለጋ ሀገራቸውን ትተው የተሰደዱ ወገኖቻችን የትውልድ መዝሙር እንዲዘምሩ ህይወት ግድ ያለቻቸው ናቸው።በወቅቱ በኢትዮጵያ በነበረው ፖለቲካ ከ108 በላይ ጋዜጠኞች በአለም ተሰደዋል።ከነሱም ውስጥ የዚህ መጽሀፍ ደርሲ አንዱ ነው።ዛሬ ለአመታት ምቹ ሁኔውታዎች በማጣት ለመሳተም ሳልችል ቀርቼ እንሆ ዛሬ የመጀመሪያዋ ልጄ ተውለደች ። በቀጣይም "ሎዛ ማሪያም " "የሎዛ ዘ ጸአት ሁለተኛ" መጽሀፍ የአውሮፓን የስደት እውነተኛ ገጽታ ታስነብበናለች። ህይወት አንዳንዴ ለመኖር የሚያስፈልግህን ያክል አትሰጠህም።ለምኖር የሚስፈልግህ "አስራምስት ብር" ቢሆን ህይወት "አምስት" ትሰጥሀለች። ቀሪዋን "አስርብር" ፍለጋ ትወጣለህ ።ወይ ታገኛታለህ ወይ አታገኛትም። የሰውልጅ በጦርነት ምክንያት እራሱን ወይም ቤተሰቡን ለማትረፍ ይሰደዳል።ጸጥታና ሰላምን ያገኛታል ወይም አያገኛትም። የሰማይ ውሀ ይነጥፍና መሬትም የውይን ፍሬዋን መስጠቷን ታቆምና ገበሬም ሞፈሩን ሰቅሎ "ውሀ" ወዳለበት ይሰደዳል። በማህበርዊ ፥ፓለቲካዊ፥ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች "ፍትህ" በማጣት የሰውልጅ ለስደት ይዳረጋል። ሰደት በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት የሰውልጅ ታሪክ ነው። የመጀመሪያው ሰው አዳም ከኤደን ያትክልት ስፍራ እግዚያብሄር አስወጣው ።የተሰደደበትን መሬት እንዲለማ አደረገው። ዘፍ፥23-24።ከአዳም ጊዜ ጀምሮ እስካለንበት ዘመን ስደት እና "ስለት" ሳይነጣጠሉ አሉ። ያቆብ በስደቱ ወቅት እንዲህ አለ፥ እግዚያብሄር-ከኔጋር ሆነህ የምሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ ፥የሚያስፈልገኝን ልብስ እና ምግብ ብትሰጠኝ ወደ አባቴ ቤትም በሰላም ብትመልሰኝ አንተ አምላኬ ትሆናለህ ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምኩት ድንጋይ ለወደፊት የእግዚያብሄር ቤት ይሆናል። ከምትሰጠኝም ከአስር አንዱን ሰጣለሁ"ዘፍ፥28 20 -22።" እንሆ "የሎዛ ዘ ጸአት" ስደተኞች ከላይ በተጠቀሱ በአንዱ ምክያቶች ተሰደዋል። ሁሉም ጸሎታቸው አንድ አይነት ነው።ሁሉም ለፈጣሪያቸው "ስለት " እያደረጉ ነው።ሁሉም ከተለያዩ የህይወት ቋት የተተፉ ናቸው። ጊዜው 2005 2006 አ.ም 1997 98 አ.ም እ.ኤ.አ ነው። ጂኦግራፊ ያልገደባቸው ናቸው፡፡ ይሳካላቸው ይሆን

0.0 (0 reviews)