ሀርሜ-ኮ

ሀርሜ-ኮ

Author/s: ዘሪሁን ገመቹ

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ለብዙ ደራሲዎች በጣም ከባዱ ነገር ስለሀገር መጻፋ አይደለም፤ በፍጽም፡፡ ስለፆታዊ ፍቅርም ገፃ ባህሪ አዎቅሮ መሳጭ ታሪክ ቀምሞ መፃፍም አይደለም የሚከብዳቸው፤ ይሄማ እንደውም ቀላሉ ስራ ነው፡፡ ስለእግዚያብሄርና ሰይጣን ተንትኖ መፈላሰፍና መራቀቅም ያን ያህል ውስብስብ አይደለም፡፡ ለአብዛኛው ፀሀፊ የኤቨረስትን ተራራ ሽቅብ በሩጫ የመውጣን ያህል ገዝፎ የሚከብደው ስለእናት መፃፍ ነው፡፡ አዎ ስለ እናት ለመፃፍ ቃላቶች ይሰንፋሉ፤ዓረፍተ ነገሮች ይከሳሉ፤ሀሳቦች ቀሊል እና ገለባ ሆነው የውስጥ ስሜትን በሙላት ለመግለጽ አቅመቢስ ይሆናሉ፡፡ይሄ የአብዛኛው ፀሀፊ ችግር ነው፡፡እንጂማ የእያንዳንዱ ደራሲ፣ ሙዚቀኛ፣ቀራፂ እና ገጣሚ የመጀመሪያ ስራ ስለእናት በሆነ ነበር:: እናት የህይወት መስታወት ብቻ ሳትሆን የተፈጥሮ አስኳልም ጭምር ነች፡፡ስለዚህ ነው ስለገዛ እናት ማውራት ከባድ የሚሆነው፡፡እኔ ግን ይሄው ደፍሬያለሁ፡፡ ስለእናቴ ላወጋችሁ ተነሳሁ፤ ስለገዛ እናቴ፡፡ እናቴ የአድባር ዛፍ ብትሆን እኔ ወንድሜ እና እህቶቼ ደግሞ እዛች የተቀደሰች አድባር ላይ የበቀልን ቅጠሎች መሆናችን አይደል?፡፡ ታዲያ የሰፈርም የሀገርም መድመቂያ ስለሆነችው ዋናዋ አድባር ማውራት ይሻላል ወይስ በማንኛውም ቀን በቅፅበታዊ የንፋስ ሽውታ ተገንጥላ መሬት በመውደቅ ልትደርቅ እና ልትከስም ስለምትችል ከንቱ ቅጠል? ባይሆን ያው ስለሙሉ የአድባሯን ታሪክ ሲያወሩ አብረው ስለቅጠሎቹም አንስቶ መወራቱ ስለማይቀር የእኛ የልጆቾ ታሪክ በእሷ ውስጥ ይጠቃለላል ብዬ አሰብኩ፡፡ በዚህ ምክንያት ለጀግንነቷ መታሰቢያነት የዚህን መፅሀፍ ርዕስ በእናቴ ስም ተሰይሟል… ‹‹ሀርሜ..ኮ›› ‹ሀርሜ-ኮ› ቃሉ የኦሮሚኛ ሲሆን ትርጉሙም ‹የእኔ-እናት› ማለት ነው፡፡ ….እናቴ የእኔ ማንነት፡፡ መልካም ንባብ ደራሲው፡፡

5.0 (1 reviews)