በጎ ኅሊና

በጎ ኅሊና

Author/s: መጋቤ ሃይማኖት ይላቅ ሻረው

Subjects

Religion, Self Development, Non Ficition, Spritual

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

በጎ ሕሊና በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የመጋቤ ሃይማኖት ይላቅ ሻረው መጽሐፍ በጣም ጠቃሚ መጽሐፍ ነው፤ እውነተኛ በጎ ሕሊና መሆኑንም ለግምገማ በተሰጠኝ ጊዜ አይቻለሁ፤ በጎ ሕሊና ልቡናችሁን አዘጋጁ፣ እዝነ ልቡናችሁን አቅኑ፣ ጠባቡን መንገድ ጥረጉ፤ የሕይወታችሁን በር አትዝጉ እያለ የሚያውጅ ቃለ አዋዲ (እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ማቴ 3÷3) ያለ መንገድ ጠራጊ መጽሐፍ ስለሆነ እንጠቀምበት እላለሁ» መጋቤ ሐዲስ ሐረገ ወይን ገነት የጅማ ሀገረ ስብከት ሰ/ት/ት መምሪያ፡፡ «በጎ ሕሊና የተሰኘውን በአስራ ስምንት (18) ምዕራፎች እና በስልሳ ሦስት (63) ንዑሳን አርዕስቶች ተዋቅሮ በመጋቤ ሃይማኖት ይላቅ ሻረው አዘጋጅነት የቀረበውን መጽሐፍ አይታችሁ እንድታቀርቡ በማለት በብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ፣ የየምና የዳውሮ፣ እንዲሁም የሰሜን ጎንደር ሀገረ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ መሠረት መጽሐፉን ተመልክተነዋል፡፡ በመሆኑም መጽሐፉ የብዙ ሊቃውንት መጻሕፍት የተጠቀሱበት እና በጥንቃቄ የተጻፈ ስለሆነ ለኅትመት ቢበቃ ዙኃኑን ያስተምራል እላለሁ፡፡» መልአከ ገነት ፍሬ ጽድቅ እንዳለው የጅማ ሀገረ ስብከት ስብከተ ሰበካ ጉባኤ መምሪያ ኃላፊ፡፡ «በጎ ሕሊና እጅግ አስፈላጊ መጽሐፍ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስም ከሁሉ አስቀድሞ ሁለት ነገሮች እንዲኖሩን አፅንቶ ይነግረናል፤ እነሱም እምነት እና በጎ ሕሊና ናቸው፡፡ (1ጢሞ 1÷19) ይህ መጽሐፍም የሕሊና ሚዛን ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡ የአንድ ሰው ማንነት ክፉ እና በጎ መሆኑ የሚታወቀው በልብ ሞልቶ የተረፈው በአንደበት ሲገለጥ ነው፡፡» (ማቴ 12÷36) መጋቤ ሃይማኖት ወንዳለም ጫን ያለው የጅማ ሀገረ ስብከት ስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ፡፡ «በጎ ሕሊና መጽሐፍ ዘመኑን የዋጀ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ ቤተሰብን፣ ሀገርን፣ ትውልድን፣ ባጠቃላይ ዓለምን ለማጣፈጥ በጎ ሕሊና ያለው ዜጋ መፍጠር አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው፡፡ በጎውን ከክፉው ለመለየት፣ የእግዚአብሔርን ልጆች ከሰይጣን አሠራር ለመጠበቅ ይህ በጎ ሕሊና የተሰኘ የመጋቤ ሃይማኖት ይላቅ ሻረው መጽሐፍ የሕሊና ብርሃን ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡» መጋቤ ሐዲስ አፈወርቅ ገነት የጅማ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ኃላፊ፡፡

0.0 (0 reviews)