ኤቶዮጵ

ኤቶዮጵ

Author/s: ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮ

Subjects

Fiction, Literature, Sociologgy

Published Year

2011 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

የኢትዮጵን የልጅነት ሰም ኢትኤልን ለዋናው ባለታሪክ ሰጥቶ እና ሌሎች ከእሱ ጋር የሚጓዙ ጽዮን፣ አብረሃም፣ ምርያም፣ ቶላ፣ ናዖድ፣ ቢታያ፣ ዘይኔና ዮሴፍ የተሰኙ ባህርያትን ፈጥሮ ታሪኩን በህክምና ትምህርት በተሰማሩ ተማሪዎች መሀል አሰናስሎ እንደ ፕ/ር እሴና ዶ/ር ሳሙኤል ባሉ ምሁሮች አጅቦ አሰገራሚዎቹ ባህታዊ፣ ወልዮችና አባ-ገዳዎች ድረስ አዎዝቶ ያዳርሰዋል። ደራሲው ከሚያነሳቸው ርእሶች ውስጥ ዛሬ የኢትዮጵያን ኅብረተሰብ የተበተበው የጥንቆላ አስከፊነት አንዱን ሰፍራ ይዟል። በተጨማሪም ገናናውን የኢትዮጵያ ታሪክና የ<ቶ> ጥበብን ይዳስሳል። ከእዚህ ሁሉ በላይ በጠቅላላው የኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች ጥንታዊ ግንኙነትና ወዳጅነት፣ እንዲሁም በእስልምና እና ክርስትና ሀይማኖቶች መሀል ያሉትን ተመሳሳይነት፣ እንድነት እና ኅብረት አጉልቶ ያንጸባርቃል። ታሪኩ ምስጢራዊ እና መንፈሳዊ ሆኖ፣ እያጓጓ እና እየተሸቆለቆለ ይፈስሳል። ቃላቱና አ/ነገሮቹም በቦታቸው ገብተው እርስበርሳቸው ተዋህደዋል። ይህን መጽሃፍ ሁሉም ሰው ቢያነበው የፈንጠዝያው (Inspiration)ን እና የአእምሮውን አድማስ ያሰፋል። (ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ)

0.0 (0 reviews)