አዲስ ሕይወት
Summary
የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ በተለያየ ሁኔታዎችና ችግሮች ውስጥ ላሉ ሰዎች ተስፋ መስጠት፣ አቅም ማጎልበትና አቅጣጫ ማሳየት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ዕርዳታ ከታከለበትም መንገድ መሪ ምርኩዝ እንዲሆን ነው፡፡ በተለይም ከራሴ ሕይወት በመነሳት ተጨባጭ የሕይወት ልምድ በማካፈል የዕይታን አድማስ ማስፋት ማስቻልነው፡፡ በምንም ዓይነት ፈተና ውስጥ ያልሆንንና ሕይወት በፈለግነው መንገድ እየሄደችልን ያለን ሰዎች ብንሆን እንኳን የሰብእናችንን ደረጃ ከፍ ለማድረግና ሁሉን ተቀብሎ የሚያሸንፍ ማንነት እንዲኖረን ይረዳናልና በፅሞና እንዲነበብ እጋብዛለው፡፡ ይህ መጽሐፍ ፈተና፣ የማሸነፍ ትግል፣ መቀበል፣ ዕይታና ተስፋ፣ አዲስ ሕይወት በሚሉ አምስት ምዕራፎች የተከፈለ ነው፡፡ በተቻለ መጠን አንዱ ከአንዱ ጋር ተያያዥነት ያለውና አንዱ የአንዱ ተከታይ ሆኖ በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ሞክሬያለሁ፡፡ የቅደም ተከተሉ ሁኔታ አከራካሪ ሊሆን ይችላል፡፡ አንባቢውም ይሆናል ብሎ በሚያምነው ቅደም ተከተል አስተካክሎ ቢያነበው ተቃውሞ የለኝም፡፡ ቀላልና ግልጽ በሆነ አማርኛ መጻፉ ሁሉም ሰው እንዲረዳው የሚያስችል ሲሆን፣ ሁሉም ምዕራፎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሕይወታችንን ዳስሰውና በጎ ተጽዕኖ ፈጥረው እንደሚያልፉ ሙሉ እምነት አለኝ፡፡