መጽሐፈ ራሤላስ

መጽሐፈ ራሤላስ

Author/s: ተስፋ ጋሻነህ

Subjects

Fiction, Religion, Self developmenty, Pilosophy

Published Year

2013 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ደራሲ፡ Samuel Johnson ትርጉም፡ ራሤላስ ጋሻነህ "ምናቡ ምክንያታዊነቱን የማይጫንበት፣ ትኩረቱን በነጻ ፍቃዱ ቁጥጥር የሚያስገዛ፣ ሀሳቦቹም እንደመሻቱ ለመምጣትና ለመሄድ የሚታዘዙለት ሰው ፈፅሞ አይገኝም፡፡ በአዕምሮው ውስጥ ድንገት ሽው የሚሉ ሃሳቦች የማያሸብሩት፣ ከተለመደው የቢሆን ዓለም ገደብ አልፎ ተስፋ እንዲያደርግ ወይም እንዲፈራ የማያስገድደው ሰው ምንኛ የተባረከ ነው? በምክንያታዊነት ላይ የሚሸፍቱ የተጋነኑ የሃሳብ ኃይላትም የእብደት ደረጃ መለኪያዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህንን ኃይል መቆጣጠርና መግራት ከቻልን ሌሎች ሰዎች ልብ ላይሉትና የአእምሮ መናጋት ምልክት ተደርጎም ላይወሰድብን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህንን የሃሳብ ኃይል በቅጡ ልንገራው ካልተቻለን በንግግሮቻችና ድርጊቶቻችን ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ ይመጣል፡፡ "ይህንን ልብወለዳዊ ሀይል ለማሞላቀቅና ለምናባችን ክንፍ በማበጀት በኩል ብዙውን ጊዜ ዋናው ስራ በፀጥታ ውስጥ ማሰላሰልን ልማዳቸው ያደረጉ ሰዎች ነው፡፡ በጥሞና መንፈስ ስንሆን ዘወትር ባተሌ አንሆንም፡፡ የማሰላሰል ተግባርም በነውጥ የተሞላ ስለሆነ ረጅም ጊዜ አብሮን የሚቆይ ጉዳይ አይሆንም፡፡ የፍላጎት ነበልባል ስሜትም ለእርጋታና ለመቦዘን መንገድ ይጠርጋል፡፡ ትኩረት አስቀያሽ ውጫዊ ጫና የሌለበት ሰው በራሱ እሳቤ ውስጥ በመሆን ደስታን መሻትና አሁን የሌለውን ማንነት ለመፍጠር በምናብ እንደገና መወለድ አለበት፡፡ በተጨማሪም ገና ሊመጣ ስላለው ነገር በውስጡ መቃተት ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ሰው አሁን ባለው ማንነቱ የረካ አይደለምና፡፡ ይህ ደግሞ ተፈጥሯዊ በረከት ነው፡፡ በመቀጠልም ገደብ በሌለው የወደፊት እሳቤ ውስጥ ክንፉን ይዘረጋል፡፡ ሊመጣ ካለው ምናባዊ ማንነቱም ከወዲሁ ያጣጥማል፡፡ በዚህ ጊዜ በአእምሮው ውስጥ የማያቋርጥ መንፈሳዊ የዳንስ ትርኢት ገቢራዊ ይሆናል፡፡ ተፈጥሮና እድል በለጋስነት ሊሰጡት በማይችሉት ደስታ ይሠጥማል፡፡ "አንዳንድ ጊዜ ልዩ የሆነ የሀሳብ ብልጭታ ሙሉ ትኩረታችንን ይሰርቅና ሌሎች የእውቀት እርካታዎችን ያኮስሳቸዋል፡፡ አዕምሯችን በመራር እውነታዎች በሚከፋበት ጊዜ፣ ከድካምና ከመቦዘን ውስጥ ወጥቶ ይህንን አዲስና ልዩ ሀሳብ በመደጋገም እውነተኛ ያልሆነውን ጣፋጭ ድግስ ይቋደሳል፡፡ ቀስበቀስ ግን ልብወለዶች ወደ እውነታዊነት ሲቀየሩ ይታያሉ፡፡ የሀሰት ሀሳቦችም የአእምሮ ክፍልን ሰንገው በመያዝ ህይወት በሀሴትና በጭንቀት ህልሞች ውስጥ ታልፋለች፡፡"

0.0 (0 reviews)