ፓስ ፓት

ፓስ ፓት

Author/s: መክት ፋንቱ (መምህር)

Subjects

Fiction

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ኢትዮጵያ ከተኛችበት ከመንቃቷና አንጡራ የእውቀት ምንጮቿን ከመጠቀሟ በፊት ወገባቸውን ጠበቅ አድርገው የማጋዝ ሥራቸውን አጠናቀው መጨረስ እንዳለባቸው ተረድተዋል። ኢትዮጵያ በድምር ከአራት ሺህ ሃምሳ አንድ በላይ የብራና መጽሐፍት በሥርቆትም ሆነ በሰበባ ሰበብ ተነጥቃለች᎓᎓ የፓስተር ዴቪድ ሀገር አሜሪካ 400 እንግሊዝ 850፣ ጀርመን 734፣ ፈረንሳይ 700፣ ቫቲካን 600፣ ኔዘር ላንድ 60፣ እስራኤል 50፣ አውስትራልያ 50፣ አርመን 30 ፣ ቤልጅየም 14፣ ካናዳ 11፣ ስዊዘርላንድ 6፣ ፓርቹጋል 4፣ ስፔን 3 እና ኒውዝላንድ 3 ይገኛሉ። ዛሬም ቢሆን ገና አረኩም᎓᎓ በተለይ ፓስተር ዴቪድ ስለ ብራና ነገር ሲሰማ ውስጡ ይንቀለቀላል። ከአባ ዕንባቆም መወዳጀቱ ደግሞ የማያልፈው ታላቅ እድል። የልባቸውን መሻት ጣል በማድረግ ህልሙን ማሳካት እንደሚችል ቅንጣት ጥርጣሬ የለውም፡፡ አንድ ቀን እንዳሻው ዘውሯቸው የሚፈልገውን በሳቸው እንደሚያሳካ ተስፈኛ ሆነ። **** "ሰውማ ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ ዕለት" ይላል። እንግዲህ ልጅም ማለት እናት ተጨንቃ ስተጠራው ፈጥኖ ከዓይኗ እንባዋን የሚያብስ ነው። እንደዚያ አይነት ልጅ መሆን መታደል ነው፡፡ እናት ሀገር ናት፣ አንድም ሐይማኖት! ልጆቼ ሰውም ልጅም ሁኑ። **** የሊቃነ ጳጳሳቱ ለፕትርክና የምረጡኝ እንቅስቃሴ ለብሄራዊ ምርጫ ይሁን ሃይማኖትን ለመምራት ግራ እስኪያጋባ ፉክክሩ ጦፈ። እንቅልፍ አጥተው ታች ላይ አበዙ። መገናኛ ብዙኀን ሳይቀሩ በጎ በጎውን ፈጣጥረውም ቢሆን ስለ ማንነታቸው እንዲያራግቡላቸው ከመወትወት በዘለለ በየጋዜጣውና መጽሔቱ በቃለ መጠይቅ ሰበብ ብቅ ብቅ እንዲሉ ለጋዜጠኞቹ መደለያ ረብጣ ረብጣውን በእስር መዠረጡ። የውስጥ ለውስጥ ሽኩቻም በዛ:: ስውር መጠላለፍ፣ ሽምቅ ውግያ ተያያዙ᎓᎓ አስመራጮች ለምርጫው ግልጽ የተቀመጠውን ሕግ፣ ደምብና ሥርዓት እየሰነጣጠቁ ለእከክህ እከከኝ የወደፊት ወሮታ ወደ ሚፈልጉት እንዲያዘነብል ለፈቃዳቸው ተረጎሙት᎓᎓ ዳጎስ ያለ እጅ መንሻም በምሥጢር እየተቀበሉ እንደሆነ እንደ ሐሜት ተሰማ። **** በዘመኑ ከተገጠመላቸው አንዱን የጎንደር ሊቃውንት የገጠሙላቸውን ግጥም፤ "ግድግዳው ቤታችሁ ያው ይሻላችኋል ካቡን አትጠጉ ይናድባችኋል" የሚለውን የግጥም ስንኝ አነበበ። አቡነ ዕንባቆምም፤ 'ምን ያለበት ምን አይችልም' ሆነው ቅኔውን እሳቸው ላይ ልክክ አድርገው ፈቱት።

0.0 (0 reviews)