አሁን ይህች ቅፅበት

አሁን ይህች ቅፅበት

Author/s: Dr. Tesfay Solomon Tsegay

Subjects

Self development, Spritual, Non Fiction

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

አሁን ይህች ቅፅበት በሚል የቀረበው መጽሃፍ በአሁኗ ቅጽበት እንዴት መኖር ብሎም ሰላም እና ደስታን ማግኘት እንደሚቻል የሚያስተምር የኤክሃርት ቶሌ መጽሐፍ ነው። መፅሃፉ አብዛኛው ስቃያችን የሚመጣው ካለፈው ጋር ካለን ቁርኝትና ስለወደፊቱ ካለን ፍርሃትና ጭንቀት ሲሆን ይህም አሁን ያለውን እውነታ እንዳንቀበል አድርጎናል። መጽሐፉ ሀሳቦቻችንና ስሜቶቻችን ማንነታችን ሳይሆኑ ከእውነተኛው ማንነታችን እና ከህይወት ምንጭ ጋር እንዳንገናኝ የሚያደርጉን ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች እንደሆኑ ያብራራል። መጽሐፉ ስለአሁኑ ጊዜ የበለጠ ለማወቅ ተግባራዊ ዘዴዎችን ያቀርባል፣ ለምሳሌ ሀሳቦቻችንን ያለፍርድ መታዘብ፣ ሁኔታዎቻችንን ያለምንም ተቃውሞ መቀበል እና በአዎንታዊ ነገሮች ላይ ማተኮር። መጽሐፉ እነዚህን ዘዴዎች በመለማመድ ራሳችንን ከአስተሳሰብ አምባገነንነት በማላቀቅ በአሁኑ ጊዜ የመገኘታችንን ደስታ እና ነፃነት ማግኘት እንችላለን ይላል። መጽሃፉ በተጨማሪ በአሁን ቅጽበት እንዴት መኖር እንዳለብንና ካለፈው ቁጭትና ህመም ብሎም ከወደፊቱ ጭንቀት እራስን ነጻ ማድረግ እንደሚቻል ያስተምራል፡፡ መጽሐፉ ራሳችንን ከሀሳቦቻችንና ስሜቶቻን በመለየት፣ አእምሮ እንዴት መከራን እንደሚፈጥር በማሳየትና ከቅርጽ እና ከግዜ በላይ የሆነውን እውነተኛ ማንነታችንን ጋር እንዴት መገናኘት እንደምንችል ያብራራል። መጽሐፉ በአሁኑ ቅጽበት የመኖር መርሆችን በተለያዩ የህይወት ዘርፎች ማለትም እንደ ግንኙነቶች፣ ጤና፣ ፈጠራ እና መንፈሳዊነት እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ተግባራዊ መመሪያ ይሰጣል። ይህንን መጽሐፍ በማንበብ የአሁንዋን ቅጽበት ኃይል እንዴት ማግኘት እንደምንችል እና በእያንዳንዷ ቅጽበት ሰላምን፣ ደስታን እና እርካታን እንደት መጎናጸፍ እንደምንችል ያስተምራል።

0.0 (0 reviews)