ኬፒአይ

ኬፒአይ

Author/s: ዝጋለ አያሌው

Subjects

Self Development, Leadership, Management, Success Factor, Non Fiction

Published Year

2015 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

‹‹ኬፒአይ›› የቢሊኒየሮች ቁልፍ እነ ቻይና እና ጃፓን በአንዴ በእድገት ጎዳና እንደ ሮኬት የተወነጨፉበት አሰራር ነው፡፡ ከሀገራችን ኢትዮጵያ የተደበቀው ‹‹ኬፒአይ›› የቢሊኒየሮች ቁልፍ ሰውን፤ጊዜን፤መርህንና መዋቅርን አገናይቶ በፍጥነት ወደ ለውጥ ጎዳና የሚመራ አሰራር ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ እንደ እኛ ሀገር ኢትዮጵያ ሲዘጋጅ፤ አይደለም ሀገርን፤ዓለምን የሚቀይር ፈጠራ ያላቸው ወጣቶች ፈጠራቸውን እንዴት አድርገው ወደ ሚጨበጥና ሚዳሰስ ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው መንገድ የሚያሳይ ነው፡፡ ሌላው እኛ ሀገር ብዙ አክሲዮኖች ኬፒአይን ባለመጠቀም የተደራጁት ሲከስሩ፤ሰበተኑ፤መንግስታዊ ተቋማት በኪሳራ ሲንቀሳቀሱ፤አዳዲስ አክሲዮኖች አንድነት እንዳይኖራቸውና እንዲጠለፉ ሲደረጉ ማስተዋል የተለመደ ነው፡፡ ኬፒአይ አሰራር ግን ለዚህ ዋና መፍትሄ ነው፡፡ እንዲሁም የወረደ የሥራ ባሕላችን ወደ ተሻለ ለውጥ እንዲመጣ የራሱን አስተዋጽኦ የሚያደርግና ለአዳዲስ ለሚዋቀሩ ‹‹የቢዝነስ›› ሀሳቦች እንዴት አድርገው፤ቢዝነስ ፕላን፤ፕሮጀክት አቀራረጽ፤ጥናታዊ ጽሑፍ አሰራርን የሚያሳይ ነው፡፡ ከማንኛውም ነገር ተጽኖ ነጻ ሀገር የምትኖረንም በኢኮኖሚው ሀቅብ ስናጎለብት ብቻ ስለሆነ ‹‹ኬፒአይ›› አሰራር በጣም አዋጭና አስፈላጊ መሆኑን የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡

0.0 (0 reviews)