በ52 ሳምንታት ሕይወትን የመለወጥ ምስጢር
Summary
እያንዳንዳቸው 52 ሳምንታዊ ለውጦች ለውጡን ማምጣት አስፈላጊ ከሆነበት ማብራርያ ጋር ነው የቀረቡት ። ለውጡን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ "የስኬት ፍኖተ ካርታ "ም አብሮ ቀርቧል። በእያንዳንዱ ሳምንት ማብቂያ ላይ ከሳምንቱ ውስጥ ስትለማመዱት በቆያችሁት አነስተኛ ለውጥ ላይ ትጠበባላችሁ ከአኗኗራችሁም ጋር ታዋህዱታላችሁ። በየሳምንቱ የምታዳብሩት ለውጥ አዲስ ከሆነባችሁ " የስኬት ፍኖተ ካርታ " በሚለው ስር የቀረቡ ጥቆማዎች ላይ አተኩሩ። ከአኗኗራችሁ ጋር ያዋሀዳችኋቸውን ለውጦች ይበልጥ ለማዳበር ደግሞ "ተጨማሪ ነጥቦች " በሚለው ስር የቀረቡት ጥቆማዎች ይረዷችኋል ። አነስተኛ ለውጦች ስኬታማ የመሆን ፍላጎታችንን ያሟላሉ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ተነስተን ነገር ግን እያንዳንዷን አነስተኛ ደረጃ ከዘነጋን ሰላም ስኬታማነት አይሰማንም ። አነስተኛ ለውጦችን ከመጣንና በእያንዳንዷ አነስተኛ ለውጥ ላይ ላስመዘገብነው ስኬት እውቅና ከሰጠን መሻሻል እያሳየን መሆኑ ይሰማናል ። ይህም ወደፊት እንድንጓዝ በአነስተኛ ለውጥ ላይ አነስተኛ ለውጥ ላይ አነስተኛ ለውጥ እየጨመርን በመጨረሻ ከትልቅ ለውጥ ላይ እንድንደርስ ይረዳናል ። ህይወትን በማስተዋል ወይም ባለማስተዋል መኖር እንችላለን ። የአስተውሎ ኑሮ ማለት በህይወታችን ውስጥ ዋና ተሳታፊ የምንሆንበት ተሞክሮዎቻችንን የምንመርጥበት እንዲሁም ለምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ሀላፊነት የምንወስድበት ኑሮ ነው ። በተቃራኒው ያለማስተዋል ኑሮ ህይወትን በዘፈቀደ በሁኔታዎች አስገዳጅነት መምራት በህይወት ላይ ቁጥጥር አለመኖር ነው ። በአስተውሎ ስትኖሩ ለምትሰሯቸው ነገሮች ትኩረት ትሰጣላችሁ ። በሰማይ መና እስኪወርድላችሁ ከመጠበቅ ይልቅ የነገሮቹ መንስኤ ለመሆን ተነሳሽነቱን ትወስዳላችሁ ። ይህም ያቀዳችኋቸውን ነገሮች ለመፈፀምና በህይወት ስኬታማ ለመሆን ያስችላችኋል ። ለምትኖሩት ህይወት ራሳችሁን ተጠያቂና ሀላፊ ማድረግ ለራሳችሁ ያላችሁን ክብር ይጨምራል ። በራሳችሁ የበለጠ እንድታምኑ ያደርጋል እንዲሁም ቀና አመለካከታችሁን ያዳብራል ።