አይ ፖሊስ

አይ ፖሊስ

Author/s: ሻምበል ተስፋዬ ርስቴ

Subjects

Fiction, Short Story, Literature

Published Year

2008 ዓ.ም

Book Type

Audio

Summary

ጋሻዉ እኮ የልጅሽ ወንድም ነዉ፡፡ ጋሻዉን ብታጠፊዉ የመጀመርያ ጠላት የሚሆንሽ የራስሽ ልጅ ነዉ ፡፡ጨካኝ አትሁኝ ፡፡ማየት ያለብሽ ትዳርሽ የተመቻቸ መሆኑን እንጂ ህጻኑ ምንም ጉዳት አያስከትልብሽም ፡፡አትቅኝ ባልሽን የያዝሽዉ አንቺ ፡፡ሴትዮዋ ምን አደረገችሽ በልጁ የተነሳ ብትፋቱኮ ልጅሽም ከእንጀራ እናት እጅ ሊወድቅ ነዉ ፡፡ ሙሉ ማዕድ ሲቀርብልሽ ግማሽ አይመርሽ ተይ ልጄ !አለቻት ፡፡ ታድያ አንድ ቀን ጥጆች ስጠብቅ ዉዬ ወደ መንደሬ ሳልሄድ ከበረት ከሌሎች ልጆች ጋር አደርኩ ፡፡ መቼም የሙጬ እንግዳን ላም ሳምነዉን የንጋቱን ላም ሰፈርን አትረሳቸዉም ፡፡ሳምነዉ ደፋር የምትፈልገዉን ተጋፍታና ነጥቃ ነበር የምትፈጽም ፡፡ ሰፈር ግን እንደ አንዳንዱ ሰዉ ሾካካ ነበረች ፡፡ አድብታና ጊዜ ጠብቃ ነበር ሰዉን ጊድራ የምትሰራዉ ፡፡አይ አፈር!ሌባ ቀማኛ አሽማቂና ጊድራ ሰሪ ነበረች ፡፡ እኔንም ከበረት ባደርኩበት በተለመደ እስስትነቷ ከእኛ ከልጆች ርቃ የተኛች መስላ ሁሉ ሰዉ ሲያንቀላፋ ሹክክ ብላ መጥታ ነጠላ ጋቢየን ከተኛሁበት ላጥ አድርጋ ወስዳ እምሽክ አደረገችዉ ፡፡ክፉ ቀበኛ !ሌሊት አብረዉኝ ከተኙ ልጆች ጋር እነርሱም እኔም ሳናዉቅ የእነሱኑ ልብስ እየተናጠቅን ስንለብስ አድረን ጧት ስንነሳ የኔ ልብስ የለም !ማን እንደወሰደዉ ብዙም አያነጋግርም ነበርና ሰፈር በላቸዉ በላቸዉ ተብሎ እኔ ሀሪቄን ሆንኩ ፡፡ ህዳርና ታህሳስ ደግሞ ያዉ ታዉቀዋለህ ብርድ ነዉ፡፡ ስለዚህ እያያ አግማስ እንደ ዶሮ ጫጩት ከራሱ ጋቢ ዉስጥ አድርጎ ጸሃይ እስክትወጣ ድረስ አብሮኝ መቀመጥ ነበረበት ፡፡አዬ መተዛዘን !አይወለደኝ አይዛመደኝ ጎረቤት ብቻ ፡፡ እናንተን ሰዉ ብዬ ከእናንተ ጋር ስሰለፍ ነዉ ጉዳዩ የተበላሳ ፡፡ያዉም ስትርበተበቱ ሴትዮዋ እንድታመልጥ አድርጋችሁ ከንቱ ድካም ካስፈጸማችሁኝ በኋላ ደግሞ ሁለት ቀን እንኳን መደበቅ ሳትችሉ ተያዛችሁ ወይኔ ምትኩ !ወይኔ ምትኩ!ወይኔ ምትኩ! ለዚህ ሁሉ ያበቃሃን አንተ ነህ !አልጠየቅንህም ተዉ አያዋጣንም እንያዛለን ብላችሁ ጥጋቡ ነህ ለዚህ የዳረግኸን ፡፡የእኛ በረኸኛ ግቤ እንኳን ሳትደርስ ተያዝህ ስግብግብ !!

0.0 (0 reviews)