ከጥቁር ሰማይ ስር

ከጥቁር ሰማይ ስር

Author/s: እንዳለጌታ ከበደ

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

ታኅሣሥ፣ 1996 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

ይህ ከ‹ጥቁር ሰማይ ሥር› (በ1996 ዓ.ም የወጣ) የአጫጭር ትረካዎች ስብስብ፣ ለደራሲው እንዳለጌታ የመጀመርያው መጽሐፉ ሲሆን፣ መጽሐፉ ሲወጣ በቋንቋ ትባቱ፣ በአተራረክ ቴክኒኩና በጭብጥ አመራረጡ፣ በጋዜጠኞችና በሥነጽሑፍ አፍቃርያን ዘንድ መወደድን ያተረፈ ኪናዊ ሥራ ስለመሆኑ ተመስክሮለት ነበር፡፡ ደራሲው አይተን እንዳላየን ባለፍናቸውና ህመም በሚጭሩ ጉዳዮች ላይ መብሰክሰኩን ያሳየበት፣ በየቤቱ ለሌላው የተቃናና ትርጉም ያለው ኑሮ ሲሉ ሥቃይ ውስጥ ስለሚገቡ ጽኑ ሰዎች ያስነበበት፣ ከከጥቁር ሰማይ ስር ውለው እያደሩ የራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የሌላውን ቀን ለማንጋት ስለሚዳክሩ ትጉሃንና ብሩሃን አጀግኖ ያሳየበት መጽሐፉ ነው፡፡ ትረካዎቹ በየጊዜው በሬዲዮ የሚተረኩና ለአጫጭር ድራማዎች የሚመረጡ ሲሆኑ፣ ከተተረኩት ሥራዎቹ መካከል በዕውቆቹ አርቲስቶቹ በእነመስታወት አራጋው እና በአበበ ባልቻ የተተረኩት ተጠቃሾችና እነዚህም በየትዩቡ የሚገኙ ናቸው፡፡

0.0 (0 reviews)