ባለ’ዳ

ባለ’ዳ

Author/s: መክት ፋንቱ (መምህር)

Subjects

Fiction, Literature

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

…ዘመን ከፍቷል። ምእመኑን ገደል እያስገባነው ያለነው እኛ ካህናቱ ነን። እንዳልኩህ ጥቂት አባቶች ይሄ ላይመለከታቸው ይችላል እንጂ አብዛኞቻችን ማለትም ከጳጳሳት ጀምሮ ለልጆቻችን ደንታ ቢስ ከሆንን ከራረምን። ብቻ ገንዘብ ያምጣ፣ ጥቅም ይኑረው እንጂ የነብሱ ነገር አያገብረንም። የሀብቱ ምንጭ ምን እንደሆነ እያወቅን ትክክል እንዳልሆነ ልንነግረው ትንፍሽ አንልም። የሚሰጠን ከሚቀር ነብሱ ትቅር ያልን እንመስላለን። መወድስ ቅኔ እንቀኝለታለን፣ ሲለንም የማእረግ ስም ከካባ ጋር እንደርብለታለን። ያኔ ምእመኑም በከንቱ ውዳሴ ነብሱ በደስታ ቅል…ጥ ትላለች። እየሸነገሉት እንደሆነ መች ተረዳ። ይገርማል! ሀገር በመሸነጋገል አለቀ! ሁሉም እንደ ደራሲ ቃላትን አስውቦና አሳምሮ ሲሸነጋገል ይውላል። አሁንማ ሽንገላ በማእረግ አድረገውታል። ሲሸነገልም ሲሸነግልም ወቃሽ ኅሊና የታጣበት ዘመን ላይ መድረሳችን እጅጉን ያሳፍራል። በተለይ በኛ በትልልቁ ደግሞ ብሷል። ደግሞኮ ዘአልቦቱ ጽልሁት እያልን ነው፡፡ ምን ማለት መሰለህ ሽንገላ የሌለበት እያልነው መሸንገላችን ኮሚክ አይደል ልጄ!” ሲሉ ፈገግ አሉ፡፡ ነገርዬው እኔን ከማሳቅ ይልቅ ማስደመሙ በዛ መሰል አጸፋ ነሳኋቸው፡፡ ከመጽሐፉ የተወሰደ

0.0 (0 reviews)