እንደዋዛ

እንደዋዛ

Author/s: መክት ፋንቱ (መምህር)

Subjects

Fiction, Literature, History, Biography

Published Year

2016 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

"እንደው አንድ አካባቢ ያለት ምን ያወጉ ይሆን? ለምሳሌ ቅድስት ሥላሴ ፕሮፌሰር አሥራትና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ አጽማቸው ያረፈው እዚሁ ግቢ ነው! ኢንጅነር ኃይሉ ሻወልም እዚሁ ናቸው። በቅርቡም ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምም ተቀላቅለዋል፣ ሌሎቹም አሉ።" ይልና ተዛምዷቸውንና ተቃርኗቸውን ለማጤን ይሞክራል። ሠናዩን ከእኩዩ፣ ቅኑን ከእቡዩ፣ ብርሃናዊውን ከጽልመታዊው ወዘተ ሲያነጻጽር፣ ሲያሰናስል ኃሊናውን ያስጨንቃል። አንዳንዶቹ በየሀውልታቸው ላይ የተጻፈላቸው መልእክትና ጥቅስ ደግሞ ትውስ ይለውና ያስፈግገዋል። ደግሞም ደሙን ያፈላዋል። የደጉ ገድል በሚጢጢ ቃላት ለኮፍ ተደርጎ ሐውልቱ ላይ እንዳልሰፈረ ለክፉውና ርጉሙ ገድል ተፈጥሮለት፣ ከምጽሐፍ ጥቅስ ተመርጦለት፣ በውብ ቃላት ተከሽኖ የጣፈጠ ስንክሳር ተደርሶለት፤ በሟች ሐውልት ላይ ሲያነብ የሚናደደው በጻፈው ላይ ነው፡፡ ማን ይጻፈው ማን ባያውቅም፤ "ምን አለበት ሟች ላይ ሙድ ባያሲዙባቸው…እኛንም ሳንወድ ባያነፍሩን! እንዲህ እንዲያ እያሉ ደ’ሞም የሞተን ባያሳሙን መልካም ነበር! አሁን ማን ይሙት ሟችን የሚያውቅ የተጻፈለትን ገድል ሐውልቱ ላይ ሲያነብ መሳቁ ይቀራል!; " ሲል ይሳለቃል። በሟችና በተጻፈው ስንክሳር መካከል ኅጠት የተግባር ዝምድና ቢያጣ። ….ሌላም ያስባል። ከዚሁ ቅጥር ከተቀበሩ ‘ልሒቃን' ራስ ሳይወርድ፤ "ዳግመኛ የመኖር አንድ እድል ቢሰጣቸው በተሰጣቸው መዋዕል ምን እናደርግበታለን ይሉ ይሆን!?" ምላሻቸውን ሲያሰላስል አንዳንዶቹን የበለጠ እንዲወዳቸው ሲያደርገው የአንዳንዶቹ ቆሽቱን እርር ድብን ያደርገዋል! ይተክናል። ድመት መንኩሳ የሚለውን ሀገርኛ ተረት ያስታውሱታል። ደገኞቹ አሁንም የተሰጣቸው ዘመን ከማክተሙ በፊት ለሀገራቸውና ለወገናቸው እንሠራለን ሲሉ ሰይጣን በእድሜ ብቻ የሚበልጣቸው ደግሞ ስላለፈው እንኳ ተጸጽተው ይቅርታ ጠይቆ፣ ከመካስ ለበቀልና ለባሰ ክፋት ሊያውሉት ምኞት ብቻ መሆኑ እያብሰለሰላቸው፤ ከመጽሐፉ የተወሰደ

0.0 (0 reviews)