በሙት መንፈስ አገር ሲታመስ

በሙት መንፈስ አገር ሲታመስ

Author/s: መቶ አለቃ አንዳርጌ መስፍን

Subjects

History, Politics, Non Ficition

Published Year

2005 ዓ.ም

Book Type

Ebook

Summary

አበዳሪ አገሮች ለጥቃቅኗ ነገሮች ለኢህአዴግ መንግስት ብር የሚያስታቅፉት አባይን የሚያህል ወንዝ ሲደፍር ለምን ብድር ከለከሉ ይህ ህዝብ ሊያዉቀዉ የሚገባ ጉዳይ ነበር ፡፡ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለዉ ግን ያባይ ግድብ ጉዳይ ድንገተኛና ጥድፊያ የሆነበት አቶ መለስ የሚያዉቁት ህዝብ የማያዉቀዉ አንድ የተደበቀ ምስጢር ይኖራል ፡፡ የሚስጥሩ ቋጠሮ ያለዉም ከዚህ ላይ ነዉ፡፡ በተረፈ አቶ መለስ እንኳንስ አባይን የኢትዮጵያን ህዝብ የደፈሩ ጀግና ናቸዉ ፡፡ታሪኩን በመቶ የቋጨ ክቡር ባንዲራዉን ‹‹ጨርቅ›› ብለዉ ያንቋሸሹ ናቸዉ፡፡ ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለዉ ግፍ እንቅልፍ አያስተኛዉም ፡፡ ሊተኛም አይችልም ፡፡ፈንጅ ላይ የተቀመጠ ድርጅት ነዉ፡፡ክፉና እኩይ በሆነዉ ተግባሩ ከህዝብ ጋር ሊስማማዉ የሚችል አንዳችም በጎ ስንቅ የለዉም ፡፡በተለይም በአማራ ህዝብ ላይ የሚዘንበዉ የክፋት ፕሮፖጋንዳና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ከምን የመነጨ ነዉ ። ኦርቶዶክስን ማጥፋት ወይንም ማዳከም የሚቻለዉ በመጀመርያ የእምነቱ ተከታይ የሆነዉ አማራ ሲመታ ነዉ በሚል ይመስላል በነዚህ 21 አመታት ዉስጥ እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ የመስቀልና የጥምቀት ዋዜማዎች እየተጠበቁ ታርዷል ። በጅማ፣ ባርካ ፣ ባሰቦት፣ የዋልድባ፣ ገዳም ሳይቀር ወደ ስኳር ኢንዱስትሪነት ኢንዲቀየር የተበየነበት የዚህ ሃይማኖቱን የመገዝገዝ ቀመር ነዉ ፡፡ ሌላዉ ሴራ ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር ለማዳማትና እስከ መጨረሻዉ ድረስ ለማቆራረጥ የኢሃአዴግ ሹሞች ሲፈጽሙ ቆይተዋል ፡፡ ከቤተክርስትያን አጠገብ መስጊድ እንዲሰራ ወይንም ካልጠፋ ቦታ ጥምቀተ ባህር የሚከበርቸዉ ቦታዎች ለመስጊድ መስርያ እየተፈቀዱ ቦታና ጊዜ እየተመረጠ መጠነ ሰፊ ደም ፈሷል ፡፡ እነዚህን ሁሉ የሚቆሰቁሷቸዉ የዘመኑ ካድሬዎች ናቸዉ፡፡ የህወሃት ሰዎች ምን እየተቀበሩ እንዳሉ ደግማችሁ ደጋግማችሁ ጠይቁ፡፡ ይህንን እኩይ ተግባር ለመገመት ወጣቱ ትዉልድ ሰንፏል ፡፡ወይንም አገራዊ ደባዉን በቅጡ የተገነዘበዉ አይመስልም ፡፡ ላባቱ ጉዳይ እናቱን የሚድር ልጅ እየተወለደ ነዉ ከመጽሃፉ ዉስጥ ገጾች የተወሰዱ

0.0 (0 reviews)